ባለሞያ ቀጥረው ለመከራከር አቅም ለሌላቸውና መንግስት ነፃ የህግ አገልግሎት የሚሰጣቸው ሰዎች
- sheger1021fm
- Nov 19
- 1 min read
ህዳር 10 2018
በፍርድ ቤቶች ጠበቃ አቁመው የህግ ባለሞያ ቀጥረው ለመከራከር አቅም ለሌላቸው ሰዎች መንግስት ነፃ የህግ አገልግሎት ይሰጣል፡፡
ነፃ የህግ አገልግሎት በተለይም በሴቶች፣ በህፃናት፣ በአካል ጉዳተኞችና በአረጋዊያን ላይ ትኩረት እንደሚያደረግ በፍትህ ሚኒስቴር የንቃተ ህግ ትምህርትና ስልጠና ዳይሬክቶሬት ከፍተኛ አቃቢ ህግ አቶ ተሰማ ግደይ ነግረዉናል፡፡
ዐቃቢ ህጉ ባለፉት 3 ወራት ውስጥ በፍትህ ሚኒስቴር 178 ፤ በጠቅላይ ፍ/ቤት ደግሞ ከ1300 በላይ ሰዎች ነፃ የህግ አገልግሎት አግኝተዋል ብለዋል፡፡

ይህም ፍትህ እንዳይጓደል፣ ድሃ እንዳይበደል፣ ሁሉም ሰው በህግ ፊት እኩል ነው የሚለውን መርህ ለማረጋገጥ እንደሚያግዝ አቶ ተሰማ ጠቁመዋል፡፡
ይሁን እንጂ ነፃ የህግ አገልግሎቱን እንዲሰጡ ሀላፊነት የሚሰጣቸው የህግ ባለሙያዎች ክርክሩን የሚያደርጉት ያለ ምንም ክፍያ በመሆኑና የፍርድ ቤት ክርክሮች ደግሞ በባህሪያቸው ውስብስብና ብዙ ድካምን የሚጠይቁ ከመሆናቸው አንፃር ፍትህን ለማስፈን እስከ ምን ድረስ ይሄዳሉ? የሚለው ለብዙዎቹ ጥያቄ ይሆናል፡፡
ከፍተኛ ዐቃቢ ህጉ አቶ ተሰማ ግደይ ግን መልስ አላቸው፡፡
ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ…
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
👇👇👇
🌐Website፡ https://www.shegerfm.com/
🎥YouTube https://tinyurl.com/37tux478
🟦Telegram https://t.me/ShegerFMRadio102_1
📘Facebook፡ https://tinyurl.com/4tx8t8wm
💬WhatsApp ፡ https://tinyurl.com/ycxjmm3s











Comments