top of page

በጋምቤላ ክልል ናፍጣ በሊትር እስከ 280 ብር እየተሸጠ ነው ሲሉ በክልሉ የተሰማሩ ባለሀብቶች ቅሬታቸውን አቀረቡ፡፡

  • Feb 24
  • 1 min read

የካቲት 17/2018  

 

በጋምቤላ ክልል ናፍጣ ከገበያው ዋጋ በላይ በሊትር እስከ 280 ብር እየተሸጠ ነው ሲሉ በክልሉ የተሰማሩ ባለሀብቶች ቅሬታቸውን አቀረቡ፡፡

 

የክልሉ ንግድና ኢንዱስትሪ ቢሮ ከአልሚዎቹ እየተነሳ ስላለው ቅሬታ አላውቅም ብሏል፡፡

 

ይህ የናፍጣ የሽያጭ በህገወጥ መንገድ ሳይሆን በግላጭ በማደያዎች እየተፈፀመ እንደሆነም ሰምተናል።

 

በነዳጅ መጨመር ምክንያትም ከ75% በላይ የሚሆን የእርሻ መሬት ፆም አዳሪ ሆኖ እንደሚከርምም አልሚዎቹ ስጋታቸውን ነግረውናል። ስራ ያቆሙ እንዳሉም ሰምተናል።

 

በዚህ ዘርፍ ለተሰማሩ አልሚዎች በታሪፉ የሚቀርበውን ነዳጅ የክልሉ ንግድ ቢሮ ከደላሎች ጋር ተመሳጥሮ እየተጠቀሙበት ነውም ብለውናል።

 

የክልሉ ንግድና ኢንዱስትሪ ቢሮ በበኩሉ አንድ ነዳጅ በ134 ብር ከ 79 ሳንቲም እንደሚሸጥ እንጂ እስከ 280 ብር እንደሚሸጥ አላውቅም ብሏል ።

 

 የጋምቤላ ክልል ንግድና ኢንዱስትሪ ቢሮ ሃላፊ አቶ ኩአንግ ኩላንግ  የነዳጅ ዋጋ ጭማሪን በሚመለከት የመጣ ቅሬታ የለም ብለዋል።

 

በኢንቨስትመንት ቢሮ በኩል የመጡ ቅሬታዎች ግን አሉ፥እሱም የነዳጅ አቅርቦትን የተመለከተ ነው ለተወሰኑት አቅርበናል ብለዋል ።

 

አልሚዎቹ ያነሱት ሌላኛው ቅሬታ  የክልሉ ንግድ ቢሮ ለእኛ በታሪፍ መቅረብ የሚገባውን ነዳጅ አስቀርቶ ከደላሎች ጋር እየተጠቀመበት ነው የሚል ነው ። 


ይህን በተመለከተም ያነሳንላቸው ሀላፊው የቀረበው ክስ መሰረተ ቢስ ነው ሲሉ አጣጥለውታል።


ሙሉ ዘገባውን ለማድመጥ…



ፍቅሩ አምባቸው


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

 

YouTube : https://shorturl.at/18TS1                   

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page