top of page

‘’በየቦታው ላለው መሬትና ለሚዘራው ሰብል የሚስማማ ማዳበርያ ለማቅረብ የሚያስችል ጥናት እየተደረገ ነው’’

  • sheger1021fm
  • 2 hours ago
  • 1 min read

ጥር 26/2018


ኢትዮጵያ ውስጥ በየቦታው ላለው መሬትና ለሚዘራው ሰብል የሚስማማ ማዳበርያ ለማቅረብ የሚያስችል ጥናት እየተደረገ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ተናገሩ፡፡


ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህን ያሉት 5ኛ ዓመት የስራ ዘመን 10ኛ መደበኛ ስብሰባ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በተካሄደበት ወቅት ነው፡፡


ከዚህ ቀደም ለሁሉም ሰብል ዓይነትና መሬት ይቀርብ የነበረው ማዳበሪያ ተመሳሳይ ነበር ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ይህን ለመቀየር መንግስት እየሰራ ነው ብለዋል፡፡


ጥናቱ ሲጠናቀቅና ወደ ስራ ሲገባ አሁን ያለው ምርት በእጥፍ እንደሚያድግም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ለምክር ቤት አባላቱ ተናግረዋል፡፡


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…


YouTube : https://shorturl.at/18TS1

WhatsApp : https://shorturl.at/8vwRx

X :- https://x.com/shegerfm?s=2

Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page