በኢትዮጵያ የኮንትሮባንድ ንግድ ከመፈታት ይልቅ ይበልጥ ውስብስብ እየሆነ መምጣቱ ተነገረ።
- Feb 24
- 1 min read
የካቲት 17/2018
በኢትዮጵያ የኮንትሮባንድ ንግድ ከመፈታት ይልቅ ይበልጥ ውስብስብ እየሆነ መምጣቱ ተነገረ።
በ5 ዓመታት ውስጥ ብቻ በኮንትሮባንድ ከኢትዮጵያ የሚወጡ ሸቀጦች ዋጋ ግምት ከ 1.3 ቢሊየን ብር ወደ 8.9 ቢሊየን ብር ማደጉ ተጠቅሷል።
በ2011 ዓ.ም 340 ሚሊየን ብር የነበረው በኮንትሮባንድ ወደ ሀገር ውስጥ የሚገቡ ሸቀጦች ዋጋ ግምት በ2015 ዓ.ም ወደ 2.74 ቢሊየን ብር ከፍ ማለቱ ተነግሯል።

የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ያዘጋጀው አራተኛው አገር አቀፍ የፀረ ህገ ወጥ ንግድ ኮንፈረንስ በስካይ ላይት ሆቴል እየተካሄደ ነው።
የቁም እንስሳት ፣ መድሃኒቶች ፣ እና ቡና የኮንትሮባንድ ንግድ በስፋት ከሚካሄድባቸው ምርቶች መካከል እንደሆነ በኮንፈረንሱ ላይ ሲነገር ሠምተናል።
ኢትዮጵያ ከሶማሊያ ፣ ጁቡቲ እና ኬንያ ጋር የምትዋሰንባቸው አካባቢዎች የኮንትሮባንድ ንግድ በስፋት የሚካሄድበት እንደሆነም ተነግሯል።

የመንግስትን ገቢ መቀነስ፣ ገበያን ማዛባት ፣ አገር በቀል ኢንዱስትሪዎችን ማቀጨጭ እና የህዝብን ጤና አደጋ ላይ መጣል ኮንትሮባንድ የሚያስከትላቸው አሉታዊ ተፅዕኖዎች ናቸው ተብሏል።
የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ህጎች እና ፖሊሲዎች የኮንትሮባንድ ንግድን መከላከል በሚያስችል መልኩ እንዲሻሻል ከመንግስት ጋር መስራቱን እንደሚቀጥል ምክትል ፕሬዝዳንቱ ዶክተር አይናለም አባይነህ በኮንፈረንሱ ላይ ተናግረዋል።
ንጋቱ ረጋሳ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
Website፡ https://www.shegerfm.com/
YouTube : https://shorturl.at/18TS1
Telegram : https://shorturl.at/68aeK
Facebook፡ https://shorturl.at/tm5Q4
WhatsApp : https://shorturl.at/8vwRx
LinkedIn: https://shorturl.at/Vfe6i
Tiktok : https://shorturl.at/lhYiv
Instagram: https://shorturl.at/9X4S7





Comments