top of page

በኢትዮጵያ ህገ መንግስት የሚነሱበት አከራካሪ ጉዳዮች

  • 24 minutes ago
  • 2 min read

የካቲት 14/2018  

 

ህገ መንግስት ይሻሻል ወይስ ባለበት ይሁን፣ በፓርላመንታዊ ስርዓት እንቀጥል ወይስ ፕሬዝዳንታዊውን እንከተል፣ የባንድራ ጉዳይ የምርጫ ሁኔታና ሌሎችም መሰል ሃሳቦች ብዙ ጊዜ የፖለቲካ ሰዎች የሚከራከሩባቸው ጉዳዮች ናቸው።

 

ህገ መንግስት ሙሉ ለሙሉ መለወጥ አለበት እና ፈጽሞ መነካት የለበትም የሚሉ የተራራቁ ሃሳቦች እንዳሉ  በተለያየ ጊዜ ሰምተናል።

 

ነገር ግን መለወጥ አለበት የሚሉ ወገኖችም ቢሆኑ የትኞቹ በሚለው ላይ ሰፋ ያለ ልዩነት እንዳላቸው ይጠቀሳል።

 

አቶ ፍሬህይወት ሳሙኤል የቀድሞ የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ምርጫ 1997 ተከትሎ በተነሳ ሁከት፣የሁከቱ አጣሪ ኮምሽን ሰብሳቢ ነበሩ።

 

አቶ ፍሬህይወት በእነዚህ አከራካሪ የህገ መንግስት ጉዳዮች ላይ መፅሐፍ የፃፉ ሲሆን አሁን ያለውን ህገ መንግስት ለማሻሻል በቂ ምክንያቶች እንዳሉ ይጠቅሳሉ።

 

ለዚህም የምርጫ ስርዓቱን እንደ አንድ ክፍተት ያነሳሉ። 

 

"ለአብነትም 10 ተወዳዳሪዎችና 10 መራጮች ቢኖሩ፣ 8 ተወዳዳሪዎች አንድ አንድ ድምፅ ኖሯቸው አንዱ ሁለት ድምፅ ስላገኘ ብቻ አሸናፊ ይሆናል፣ ይህም አንድ ተወዳዳሪ 8 ተቃዋሚ እያለው 2 ድምፅ ስላገኘ ብቻ  በምርጫ የሚያሸንፍበት ስርዓት ትክክል አይደለም" ይላሉ።

 

አቶ ፍሬህይወት ሌለኛው አሁን በስራ ላይ ያለው ህገ መንግስት ክፍተት ብለው የሚያነሱት አንቀፅ 39 ነው።

 

በአንቀፅ 39 ላይ ያለውና ያለገደብ የመገንጠልን መብት የሚሰጠው አንቀፅ በየትኛውም ዓለም ላይ የሌለ በሀሳብ እንጂ በተግባር መሬት ላይ መውረድ የማይችል ነው ይላሉ።

'ከ80 በላይ ብሔር ብሔረሰቦች ያሉባት ኢትዮጵያ የዚህን ህገ መንግስት መብት ቢጠቀሙ 80 ትናንሽ ሃገራት ሊፈጠሩ ነው ወይ? ይህ እንዴት ሊሆን ይችላል?" ሲሉም ይጠይቃሉ።

 

የማንኛውም ሀገር ህገ መንግስት ፍፁም የተሟላ አይደለም የሚሉት አቶ ፍሬህይወት የኢትዮጵያ ህገ መንግስትም ለማሻሻያ ሀሳብ፣ጠረጴዛ ላይ መቅረብ አለበት የሚል ሃሳብ አላቸው።

 

ይሁን እንጂ አሁን ባለው ሁኔታ ህገ መንግስቱን በማሻሻል ሂደት ውስጥ ያልሰለጠነ በአጋላይነትና በመወቃቀስ ላይ የተመሰረተ የፖለቲካ ባህላችን ትልቅ ተግዳሮት ሆኗል ይላሉ።

 

አቶ ፍሬህይወት ህገ መንግስቱ ራሱ ህገ መንግስቱ እንዳይሻሻል ሌላ ፈተና እንደሆነ ያስረዳሉ።

 

ለዚህም ህገ መንግስቱ ሁሉም ክልሎች ሙሉ በሙሉ ያለምንም ተቃውሞ ካልተስማሙበት በቀር የማይሻሻሉ አንቀፆች እንዳሉ ደንግጓል ይላሉ።

 

ለአብነትም አስር ክልሎች እንዲቀየር ፈቅደው አንድ ክልል ባለመፈለጉ ብቻ  የብዙሃኑ  ፍላጎት፣በአነሳው ፍላጎት ስር መውደቁ ዴሞክራሲያዊ ስርዓትን እንደማያሳይ ያስረዳሉ።

 

ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ….

 

የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

 

YouTube : https://shorturl.at/18TS1                   

Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page