ሰዎች ከንብረታቸው ላይ ለልማት በሀይል እንደሚነሱ፣ የእንባ ጠባቂ ተቋም ሪፖርት ተናገረ።
- 2 hours ago
- 2 min read
ሰኔ 18/2018
ሰዎች ከንብረታቸው ላይ ለልማት በሀይል እንደሚነሱ፣ በወቅቱ ካሳ እንደማይከፈላቸው እና ከንብረታቸው ላይ ሲነሱ ስለ ልማቱ አስቀደሞ ውይይት ከባለመብቶች ጋር እንደማይካሄድ የህዝብ አንባ ጠባቂ ተቋም 11 ወራት ሪፖርት ተናገረ።
ዛሬ በፓርላማው መደበኛ ሰብሰባ ላይ ያቀረበው የተቋሙ የ11 ወራት ሪፖርት ሰነድ አንዳንድ የጤና ተቋማት የጤና መድን ተጠቃሚዎችን መድሃኒት የለም አንደሚሏቸው ነገር ግን እዛው ለሚከፍሉ ታካሚዎች መዳኒቶችን እንደሚሸጡ አረጋግጫለሁ ብሏል።
በ14 ገጽ ተሰናድቶ በህዝብ ተወካዮች መክር ቤት መደበኛ ሰብሰባ ላይ የቀረበው ይህ የስራ ክንውን ሪፖርት እንባ ጠባቂ ተቋም በለፉት 11 ወራት 1715 አቤቱታዎችን ከ44 ሺ900 በላይ ሰዎች መቀበሉን አስረድቷል።
ተቋሙ ለህዝብ ጥቅም ሲባል የመሬት ይዞታ የሚለቀቅበት እና ለንብረት ካሳ የሚከፈልበትን ሁኔታ አስመልክቶ ተግባራዊ እየተደረጉ የሚገኙ የህግ ማዕቀፎች እንዲሁም አሰራሮች ላይ "ስልታዊ" ያለውን ምርመራ ማካሄደን ጠቅሷል።

በዚህም ተነሺዎች ከመነሳታቸው በፊት ቢያንስ ከአንድ ዓመት በፊት ስለ ልማቱ አይነት ፣ጠቀሜታ እና አጠቃላይ ሂደት እንዲያውቁ አለመደረጉን ሪፖርቱ ጠቁሟል ።
እንዲለቁ በተወሰነው ቦታ ከሚገኘ ተነሺዎች ካሳ የሚከፈልባቸውን ንብረቶች የልኬት መጠን መረጃ አለመሰብሰቡ እና ሊከፈላቸው የሚገባው ካሳ አንዳልተወሰንም እንባ ጠባቂ በሪፖርቱ ተናግሯል ።
በተጨማሪም ካሳ እንዲከፈላቸው ከተወሰነ በኋላም ሳይከፈላቸው "አመታት "ሊፈጅ አንደሚችል ማወቁን ጠቅሷል፡፡
ባለመብቶቹ በሀይል ከተነሱ በኋላ መብታቸውን ለማስከበር በተለያዩ ተቋማት አቤቱታ ለማቅረብ መገደዳቸውን የእንባ ጠባቂ ተቋም ሪፖርት ያሳያል፡፡
የህዝብ አንባ ጠባቂ ተቋም ሰዎች ከንብረታቸው ላይ ለልማት በሃይል እንደሚነሱ ፣በወቅቱ ካሳ እንደማይከፈላቸው እና ከንብረታቸው ላይ ሲነሱ ስለ ልማቱ አስቀደሞ ወይይት ከባለ መብቶች ጋር እንደማይካሄድ ባስረዳበት ሪፖርቱ የተጠቀሱት ድርጊቶች የተፈጸሙበትን ቦታም ሆነ ጊዜ አልጠቀሰም፡፡
ድርጊቱ ግን ለሕዝብ ጥቅም ሲባል የመሬት ይዞታ የሚለቀቅበት፣ ካሳ የሚከፈልበት እና ተነሺዎች መልሰው የሚቋቋሙበትን ሁኔታ ለመወሰን የወጣ አዋጅን በግልጽ የሚቃረን እንደሆነ ተቋሙ አስረድቷል፡፡
ከመድሃኒት አቅርቦት ጋር በተያያዘ ደግሞ በተሰራ የቁጥጥር ስራ በአንዳንድ የጤና ተቋማት ክፍያ ለሚፈጽሙ ታካሚዎች መድሃኒት ሲቀርብ ለጤና መድን ተጠቃሚዎች መድሃኒት እንደሌለ ይነገራቸዋል ብሏል፡፡
በዚህም ምክንያት ተገልጋዮች ለተጨማሪ ወጪና እንግልት እየተዳረጉ እና ለአስተዳደራዊ በደል እየተጋለጡ እንደሆነ ሪፖርቱ ዘርዝሯል፡፡
በጤና ተቋማት የቅሬታ አቀራረብ ሥርዓት እንዳለ የጠቀሰው የጠቋሙ ሪፖርት ነገር ግን ግልጽ የሆነ የአሠራር ሂደት ባለመዘርጋቱ ቅሬታቸውን በቀላሉ ማቅረብ አልቻሉም ብሏል፡፡
የማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን አባላትና ቤተሰቦቻቸው የማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድን ተቋሙ በሚያቀርባቸው የጥቅም ማዕቀፎች ውል ከተያዘባቸው ጤና ተቋማት ያለ ክፍያ የማግኘት መብትእንዳላቸው የህዝብ እንባ ጠባቂ ጠቋም አሰረድቷል፡፡
ይሁንና መድሃኒት በአይነትና በመጠን እየቀረበ ባለመሆኑ የማህበረሰብ ጤና መድህን ተጠቃሚው ህብረተሰብም ሆነ በግሉ የሚታከመው ማህበረሰብ ተገቢውን አገልግሎት እያገኘ ባለመሆኑ ለከፋ ወጪና እንግልት እየተዳረገ ስለሆነ የተለዩ ክፍተቶች በቀጣይ እንዲታረሙ በምክረ-ሃሳቡ ሰጥቷል፡፡
በደቡብና ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልሎች አንዳንድ ወረዳዎችና ከተማ አስተዳደሮች ለተለያዩ የልማት ስራዎች እና ለማህበራዊና አገልግሎቶች በሚል ከሰራተኞች ያለፍቃዳቸው ደሞዝ እንደሚቆረጥባቸው እንባ ጠባቂ አረጋግጫለሁ ብሏል፡፡
ድርጊቱ ከሕግ አግባብ ውጪ ነውና ያለሰራተኞች ፈቃድ ደምወዛቸው መቁረጥ ተገቢ እንዳልሆነ አሳስቧል፡፡
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል አንድአንድ ወረዳዎች ደግሞ ከህግ ውጪ በአንድ የሰራ መደብ መታወቂያ ቁጥር ላይ ከአንድ በላይ ቅጥር መፈፀሙን አሳውቋል፡፡
ያሬድ እንዳሻው




Comments