top of page

በአየር ንብረት ለውጥ፣ ስርዓተ ምግብና ስርዓተ ፆታ ተፅዕኖ ምክንያት የሚፈጠሩ ችግሮች ለመፍታት ሶስቱንም በአንድ ላይ መስራት ይገባል ተብሏል፡፡

  • sheger1021fm
  • 2 days ago
  • 2 min read

ታህሳስ 14/2018


በአየር ንብረት ለውጥ፣ ስርዓተ ምግብና ስርዓተ ፆታ ተፅዕኖ ምክንያት የሚፈጠሩ ችግሮች እርስ በርስ የተሳሰሩ በመሆናቸው ችግሩን ለመፍታት ሶስቱንም በአንድ ላይ መስራት ይገባል ተብሏል፡፡


በአየር ንብረት ለውጥ ችግር ምክንያት የስርዓተ ምግብ መዛባት ይከሰታል፤ በዚህ ምክንያት የሚመጣው የምግብ እጥረትና ሌላውም  ችግር ይበልጡን ሴቶችና ህፃናት ላይ እንደሚበረታ ጥናት አሳይቷል፡፡


የማህበራዊ ጥናት መድረክ (ፎረም ፎር ሶሻል ስተዲስ) በቀረበ ጥናት በአንደኛው ምክንያት የሚፈጠረው ችግር ሌላኛውን እያባባሰው ነው፤ ይሁንና ይህንን በአንድ አስተባብሮ የሚሰራ ተቋም በጣም ጥቂት መሆኑ ታይቷል ብሏል፡፡ 


ተቋሙ ለ1 ዓመት ከ6 ወራት ያህል ጂካን (GCAN) በተባለው ፕሮጀክት በከወነው በዚህ ጥናት ላይ ጉዳዩ ይመለከታቸዋል የተባሉ 15 ተቋማት መሳተፋቸውን የነገሩን በፎረም ፎር ሶሻል ስተዲስ የጂካን ፕሮጀክት አስተባባሪና በጥናቱ ከተሳተፉት መካከል የሆኑት  ሰላም ኢሳያስ (ዶ/ር) ናቸው፡፡


ree

በተለይ በመንግስት ተቋማት እነዚህ ሶስቱንም ጉዳዮች በአንድ አስተባብሮ የሚሰራ ባለሙያ እጥረት የተፈጠረው በአብዛኛው ባለሙያዎቹ አንዱ መስክ የሰረጠኑ ስለሚሆኑ፣ ያሉት ባለሙያዎችም ቢሆኑ ለተሻለ ገቢ በሚል በብዛት ተቋሙን ስለሚለቅቁ፤ በአየር ንብረት ለውጥ፣ ስርዓተ ምግብና ስርዓተ ፆታ ተፅዕኖ ምክንያት የሚፈጠሩ ችግሮችን ከመሰረቱ እንዳይፈቱ ማድረጉን ጥናቱ አሳይቷል ያሉን ሌላው በጥናቱ የተሳተፉትና በአለም አቀፉ የፖሊሲ ምርምር ኢንስቲትዩት ተመራማሪ የሆኑት ታደሰ ዘርፉ (ዶ/ር) ናቸው፡፡

ree

ስለ ጉዳዩ ያስረዱት የህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት አባል በስራችን ያሉ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች እነዚህን ጉዳዮች በአንድ ላይ አይሰሩም ከዚህ አንፃር የምንሰጣቸው ምክረ ሃሳቦች አይተገበሩም ይላሉ፡፡


ሁሉንም የችግሩ መንስኤዎች አካቶ የሚሰራ ባለሙያ ለማፍራት ካሪኩለሞችን  መከለስ፣ስልጠናዎች መስጠት ያስፈልጋል የሚለው በጥናቱ በምክረ ሃሳብነት ቀርቧል፡

ree


ተቋማት የአየር ንብረት ለውጥን፣ስርዓተ ምግብነረና ስርዓተ ፆታን እንዴት አስተሳስረው ይስሩ? የሚለውም ትኩረት ተሰጥቶታል ብለውናል ተመራማሪው ታደሰ ዘርፉ (ዶ/ር)፡፡


በፎረም ፎር ሶሻል ስተዲስ የጂካን ፕሮጀክት የተከወነው ጥናቱ በፖሊሲ ደረጃ ያሉ ችግሮችን ለመለየት የተከወነ ሲሆን ጥናቱን ምን ያህል እውነት ነው የሚለውን ለማወቅ ይመለከታቸዋል ካላቸው ተቋማት ጋር አጥኚው ተቋም ተወያይቷል፡፡


ምንታምር ፀጋው


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

  

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page