ወባ ስርጭትን ከአፍሪካ በፈረንጆቹ 2030 ለማጥፋት በአፍሪካ ህብረት የተያዘውን ግብ ለማሳካተት የሚያስችል ስራ አባል አገራት እየሰሩ እንዳልሆነ ተነገረ።
- 1 hour ago
- 1 min read
የካቲት 9/2018
ወባ ስርጭትን ከአፍሪካ በፈረንጆቹ 2030 ለማጥፋት በአፍሪካ ህብረት የተያዘውን ግብ ለማሳካተት የሚያስችል ስራ አባል አገራት እየሰሩ እንዳልሆነ ተነገረ።
በፈረንጆቹ 2030 የወባን ስርጭት ከአህጉሪቱ ወደ ዞሮ ለማውረድ ግብ ተቀምጦ የነበረ ቢሆንም የበሽታው ስርጭት መጠን እና በህመሙ በሚሞተው ሰው መጠን አፍሪካ አሁንም ከአለም ቀደማሚውን ስፍራ ትይዛለች።

በአለም ጤና ድርጅት ሪፖርት መሰረት በ 2024 በአለም አቀፍ ደረጃ ካለው የወባ ስርጭት ወይንም የተጠቂ መጠን 96 በመቶ ወይንም ከ270 ሚሊዮን በላይ በአፍሪካ ሲሆን ፤በበሽታው ሕይወቱን ከሚጣው የአለማችን ህዝብ ደግሞ 97 በመቶ በአፍሪካ ህብረት አባል አገራት የሚመዘገብ መሆኑን ይዘረዝራል።
የ2025 የአፍሪካ የወባ ህመም ክትትል ሪፖርት እንደሚያሳየው 270 ሚሊየን በላይ የአህጉሪቱ ዜጎች በህመሙ የተያዙ ሲሆን ከነዚህ ወሰጥ ወደ 600ሺ የሚጠጉት ደግሞ ሕይወታቸውን አጥተዋል።
በ39ኛው የህብረቱ የመሪዎች ጉባዔ ጎን ለጎን የአህጉሩን የ2025 የወባ ስርጭት መከላከል ሂደት ምን ላይ እንደሚገኝ ገልጻ ያደረጉት የአፍሪካ መሪዎች የወባ ስርጭት መከላከል ጥምረት ሊቀመንበር ዱማ ጌዲዮን ቦኮ ስርጭቱን ለመግባታት ፈጣን እርምጃ ካልተወሰደ አህጉሪቱ ለበርካታ ዓስርት ዓመታት በሽታዉን ለመቆጣጠር ያስመዘገበችውን ስኬት እንዳታጠው አስጠንቅቀዋል።
በሽታውን ለመቆጣጠር የሚደረገውን ጥረት የሚደግፉ ለጋሾችም በእጅጉ ማሽቆልቆላቸውን ዓመታዊ ሪፖርት ጠቁሟል።
ይህም ከአየር ነብረት ለውጥ ፣ከተፈናቃይዎች መጨመር ፣ከዋጋ መናር እና እየጨመረ ከመጠው የሰብዓዊ አቅርቦት ቀውስ ጋር ችግሩን በእንቅረት ላይ ጆሮ ደግፍ አድርጎታል።
የህብረቱ አባል አገራት ስርጭቱን እና ጥፋቱን ለመቀነስ ከውጭ አገሩት እና አገሩስጥ ድጋፍ እንዲፈላልጉ፣ስርጭቱን ለመግታት የሚረዱ ስራዎች ላይ መዕዋለ ነዋያቸውን እንዲፈሱ እና ከበሽታ ነጻ ለመሆን የሚረዱ ስራዎች ላይ እንዲተኩሩ የአፍሪካ መሪዎች የወባ ስርጭት መከላከል ጥምረት ሊቀመንበር ዱማ ጌዲዮን ቦኮ አሳስበዋል።
ያን ማድረግ የማይቻል እና በቂ ድጋፍ ማግኘት የማይቻል ከሆነ ግን በ2030 በአህገሩ ዓመታዊ ጥቀል ምርት ላይ ወይንም GDP ላይ 30 ቢሊዮን ዶላር ኪሳራ ሊያደርስ ይችላል ብሏል ዓመታዊ ሪፖርቱ።
ሙሉ ደጋፉ የሚገኝ ከሆነ ደግሞ የአፍሪካን ኢኮኖሚ በመጪዎቹ 15 ዓመታት ውስጥ በ140 ቢሊዮን ዶላር ክፍ ሊያደርግ ይችላል ሲል ዘርዝሯል።
ያሬድ እንዳሻው








