top of page

ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ በሰሜኑ ጦርነት የኤርትራ ሰራዊት በትግራይ ወጣቶችን መጨፍጨፍና ኢንዱስትሪዎችን መዝረፉን እንዲቆም ኢትዮጵያ መንግስት 2 ጊዜ ወደ ኤርትራ ልዑክ ልኮ እንደነበር ይፋ አደረጉ፡፡

  • sheger1021fm
  • 2 hours ago
  • 1 min read

ጥር 26/2018


ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በሰሜኑ ጦርነት የኤርትራ ሰራዊት በትግራይ ክልል ወጣቶችን መጨፍጨፍ  እና ኢንዱስትሪዎችን መዝረፉን እንዲቆም ኢትዮጵያ መንግስት ሁለት ጊዜ ወደ ኤርትራ ልዑክ ልኮ እንደነበር ይፋ አደረጉ፡፡


ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ይህን ይፋ ያድጉት  ዛሬ በፓርላማ በነበራቸው ቆይታ ነው።


ጠቅላይ ሚኒስትሩ አንዳንድ ሰዎች  በኢትዮጵያ እና ኤርትራ መካከል ችግር የተፈጠረው  የኢትዮጵያ መንግስት የቀይ ባህር ጥያቄ ስላነሳ ነው ብለው ያስባሉ ፣ ይተነትናሉ ግን አይደለም ብለዋል።


ጸቡ የተጀመረው የቀይ ባህር ጉዳይ ሲመጣ አይደለም ፤"በትግራይ ውጊያ ሲጀመር የመጀመሪያ ዙር ውጊያ ሽሬን ካስለቀቅን በኋላ የኤርትራ ጦር ከኋላ ኋላ ተከትሎ ሽረ ገብቶ የግለሰቦችን ቤት ማፍረስ ሲጀምር ጸብ ተጀምሯል ፣አክሱም ገብተን ስናልፍ አክሱም ግብቶ ወጣቶችን በጅምላ ሲረሽን ጸብ ተፋፍሟል ፤ አድዋን ይዘን ስናልፍ አደዋ ሄዶ ፋብሪካዎችን ሲፈታታ ፣ ሲሰርቅ ጸብ ተጋግሏል"ሲሉ አስታውሰዋል፡፡

"አዲግራት ደርሰን የመዳኒት ፋብሪካውን የሚነቀለውን ነቅለው የማይነቀለውን ሲያፈራርሱ ጸቡ ከጨፍ ደርሷል፤ ግን የኢትዮጵያ መንግስት ያኔ በዚህም በዚያም ለመዋጋት በቃት አንበረውም "ብለዋል።


ውስን ሃይል ስለነበርን በውቅቱ  የያዝነውን እያጸናን አንሄድም ነበር ግን ይህ ጉዳይ ለዛሬ ዋጋ የለውም ለታሪክ ግን ማንሳት የምፈልገው ጉዳይ "አክሱም ወጣቶች ሲገደሉ፣ አደዋ ሲዘረፍ፣ አዲግራት ሲዘረፍ" በርካታ ልዑክ ወደ ኤርትራ ልኬያለሁ ሲሉ ዐቢይ አህመድ ተነግረዋል ።


የላኳቸው ሰዎች ገሚሱ እሁን ከእኛ ጋር የሉም ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለምሳሌ በወቅቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የነበሩት አቶ ገዱ አንዳርጋቸውን ከአንዴም ሁለቴ ኤርትራ ልክያችዋለሁ ።


የላኳቸውም የትግራይ  ህዝቡን አታጎሳቅሉ ፣ሃብቱንም አትዘረፉ ጸቡም ከሕወሓት እንጂ ከህዝቡ አይደለም በሚል ነው ብለዋል።


አቶ ደመቀ መኮንንም ከተላኩት ልዑካን ውስጥ መሆናቸው ጠቅላይ ሚኒስትሩ አስታውሰዋል፡፡


በወቅቱ ቸግሮን የነበረው ጉዳይ እኛ የለቀቅነውን የትግራይ  ከተሞች እነሱ ከኋላ ይገባሉ መቀሌ ስንገባ ተከትለውን ገብተው ጉዳት ያስከትላሉ፡፡


ከዚህ በኋላ ውቅሮን ካለፋቹ ፀቡ የሚሆነው ከእኛ ጋር ነው ብለናቸው ነው ያልመጡት ሲሉ አስረድተዋል፡፡


ያሬድ እንዳሻው

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page