top of page

በባንኮችና በሌሎችም ዘርፎች እንደተደረገው ለውጭ አየር መንገዶች ዘርፉን የመክፈት ፍላጎት መንግስት ለጊዜው የለውም ተባለ፡፡

  • Feb 23
  • 1 min read

የካቲት 16/2018


በባንኮችና በሌሎችም ዘርፎች እንደተደረገው ለውጭ አየር መንገዶች ዘርፉን የመክፈት ፍላጎት መንግስት ለጊዜው የለውም ተባለ፡፡


በኢትዮጵያ የሚሰሩ የግል አየር መንገዶች ብዛት 12 ቢደርስም እነደ ኬኒያ እና ኡጋንዳ ካሉት የጎረቤት ሀገራት ጋር ሲነፃፀር ግን በአቅምም በቁጥርም ዝቅተኛ ነው ይባላል። እነዚህ የግል አየር መንገዶች(General Aviation) ዘርፉ ጠንክሮና እራሱን ችሎ መቆም እስከሚችል ድረስም መንግስት የውጭ ሀገር አየር መንገዶችን የመጋበዝ ፍላጎት የለውም ተብሏል።


የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ዮሃንስ አበራ እንደነገሩን በሂደት ግን በሩ ለውጭ ባለሃብቶች ክፍት መሆኑ አይቀርም።


በኢትዮጵያ በግል አየር መንገድ የተሰማሩ ኩባንያዎች ከህግ እስከ አሰራር የሚያነሷቸው ብዙ ችግሮች እንዳሉ ይነሳል። ዋና ዳይሬክተሩ የሚበዙት ችግሮች በሂደት እየተፈቱ መሆኑን ጠቅሰው እንደ ምሳሌም አውሮፕላንን መያዣ አድርጎ ከባንክ ገንዘብ መበደር የተፈቀደው በቅርብ ጊዜ መሆኑን አንስተዋል። ሌሎች ተመሳሳይ የዘርፉ ችግሮችም እየተፈቱ ነው ብለዋል።


በቅርብ ጊዜ ውስጥም ተጨማሪ ሁለት ኩባንያዎች በግል የአቪዬሽን ዘርፍ ለመግባት በዝግጅት ላይ መሆናቸውንም ነግረውናል።


በተለይ አንደኛው አውሮፕላኖችን እያስመጣ በአፍሪካ ሀገራት እያከራየ ለመስራት በዝግጅት ላይ ነው ተብሏል።


ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ……


ቴዎድሮስ ወርቁ


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…


YouTube : https://shorturl.at/18TS1

WhatsApp : https://shorturl.at/8vwRx

X :- https://x.com/shegerfm?s=2

Recent Posts

See All
ከህዳሴ ግድብ ከ11 ሚሊዮን ኪሎ ግራም በላይ ዓሣ ተመረተ፡፡

ሐምሌ 21 2018 ከህዳሴ ግድብ ከ11 ሚሊዮን ኪሎ ግራም በላይ ዓሣ ተመረተ፡፡ የዓሣ ምርቱ ወደ መሃል ሃገር እየተጫነ ለአዲስ አበባ ገበያ እየቀረበ ነውም ተብሏል፡፡ ታላቁ የህዳሴ ግድብ መገንባቱን ተከትሎ በተፈጠረው ንጋት ሰው ሰራሽ ሃይቅ በኢትዮጵያ ትልቁና ከ70 በላይ ደሴቶች ያሉት የውሃ አካል ነው፡፡ ከቅርብ

 
 
 
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት 30.65 ቢሊዮን ዶላር የሚጠይቅ የኃይል ማስፋፊያ ዕቅድ ይፋ አደረገ።

ሐምሌ 20 2018 የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት 30.65 ቢሊዮን ዶላር የሚጠይቅ የኃይል ማስፋፊያ ዕቅድ ይፋ አደረገ። እቅዱ የኔትወርክ ማሻሻያ እና ማስፋፊያ፣ የሰብስቴሽን እና ተያያዥ የመሰረተ ልማት ግንባታዎች፣ ስማርት ግሪድ እና ቆጣሪ ማስፋፋትን እንደሚያካትት አገልግሎቱ ዛሬ ይፋ አድርጓል፡፡ የኢትዮጵያ ኤሌ

 
 
 

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play
  • Facebook
  • X
  • Youtube
  • TikTok
  • Telegram
  • Whatsapp

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page