top of page

በበጀት ዓመቱ ሰባት ወራት ከ800 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ተናግረዋል።

  • sheger1021fm
  • 1 hour ago
  • 1 min read

ጥር 26/2018


በበጀት ዓመቱ ሰባት ወራት ከ800 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ተናግረዋል።


በአጠቃላይ በጀት ዓመቱ 1 ነጥብ 2 ቢለየን ብር ገቢ ለመሰብሰብ እንደታቀደ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት አባላት ማብራሪያ ሲሰጡ ተናግረዋል።


የሰባት ወራቱ አፈጻጸም የዓመቱ ዕቅድ ቀድሞ እንደሚሳካ የሚያመለክት ነው ብለዋል።


ያለውን አፈጻጸም ተከትሎ በፌዴራል ደረጃ የተቀመጠውን የ1 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር ዕቅድ ወደ 1 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር የማሳደግ ሃሳብ እንዳለ ጠቅሰዋል።


ክልሎች የሚሰበስቡትን ገቢ ደግሞ 1 ትሪሊየን ብር እንዲደርስ መታሰቡን አመልክተዋል።


በዚህም በአጠቃላይ 2 ነጥብ 5 ትሪሊየን ብር በመሰብሰብ ከአጠቃላይ ጥቅል ሀገራዊ ምርት ወይም ጂ ዲ ፒ ዘጠኝ በመቶ ድርሻ የሚይዝ ገቢ እንዲኖረን እየሰራን ነው ሲሉ አክለዋል።


ኢትዮጵያ እስከ አሁን የምትሰበስበው ገቢ ከአጠቃላይ ጥቅል ሀገራዊ ምርት ወይም ጂ ዲ ፒ ድርሻው ሰባት በመቶ እንደሆነ ጠቅላይ ሚኒስትሩ አስታውሰዋል።


የታክስ መሰረትን መስፋት እና ኦቶሜሽን ላይ የተሰራው ስራ የሚሰበሰበው ገቢ እንዲያድግ አስተዋጽኦ ማድረጋቸውን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተናግረዋል።


በበጀት ዓመቱ ስድስት ወራት መንግስት 801 ቢሊየን ብር ወጪ ያደርጋል ተብሎ ታቅዶ እንደነበር ያስታወሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወጪ የሆነው ግን የዕቅዱ 48 ነጥብ 5 በመቶ ነው ብለዋል።


ንጋቱ ረጋሳ


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…


YouTube : https://shorturl.at/18TS1

WhatsApp : https://shorturl.at/8vwRx

X :- https://x.com/shegerfm?s=2

Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page