በሰው ሰራሽ እና ተፈጥሯዊ ምክንያቶች ተማሪዎች ከትምህርት ገበታቸው ርቀው ቆይተዋል፡፡
- sheger1021fm
- 2 hours ago
- 1 min read
ጥር 25/2018
በሰው ሰራሽ እና ተፈጥሯዊ ምክንያቶች ተማሪዎች ከትምህርት ገበታቸው ርቀው ቆይተዋል፡፡
በኢትዮጵያ በሚሊየን የሚቆጠሩ ተማሪዎች ለተከታታይ 3 ዓመታት እና ከዚያ በላይ ለሚሆን ጊዜ ከትምህርት ገበታቸው ላይ አልነበሩም፡፡
በተለይ በአንዳንድ የሀገሪቱ አካባቢዎች በነበሩ አሁንም ድረስ በቀጠሉ የሰላም እጦቶች ተማሪዎች ቀያቸውን ለቀው ወጥተዋል፣ ትምህርት ቤቶች በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ ወድመዋል፡፡
በዚህም ምክንያት ልጆች ከእስክርቢቶ እና ደብተር እርቀው ሰንብተዋል፤ በሚሊየን የሚቆጠሩ ተማሪዎችም ከትምህርት ቤት በራፍ ሳይደርሱ ከርመዋል፡፡
ልጆች ከትምህርት ገበታ መራቃቸው ሊያገኙት የሚገባቸውን እውቀት እና ሊያውቋቸው የሚገቡ ነገሮችን ይነፈጋሉ ይህ ደግሞ በተለያየ መንገድ ተፅእኖውን ያበረታዋል ተብሏል፡፡
በሀገር አቀፍም ሆነ በግለሰብ ደረጃ ሊያስከትለው የሚችለው ችግር ቀላል የሚባል እንዳልሆነ የሚነገር ሲሆን ጉዳቱን አሁንም እየተመለከትነው ነው ተብሏል።
ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ…..
ፍቅሩ አምባቸው
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
Website፡ https://www.shegerfm.com/
YouTube : https://shorturl.at/18TS1
Telegram : https://shorturl.at/68aeK
Facebook፡ https://shorturl.at/tm5Q4
WhatsApp : https://shorturl.at/8vwRx
LinkedIn: https://shorturl.at/Vfe6i
Tiktok : https://shorturl.at/lhYiv
Instagram: https://shorturl.at/9X4S7












Comments