በሀገር አቀፍ የምክክር ጉባዔ ላይ የሚመከርባቸው አጀንዳዎች መሰረታዊ የሆኑ 10 ጉዳዮች ላይ ነው ተባለ።
- 3 hours ago
- 1 min read
ሰኔ 13/2018
በሀገር አቀፍ የምክክር ጉባዔ ላይ የሚመከርባቸው አጀንዳዎች መሰረታዊ የሆኑ 10 ጉዳዮች ላይ ነው ተባለ።
ይህን ያሉት የምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነር አምባሳደር መሀመድ ድሪር ዛሬ ሰኔ 13 ቀን 2018 ዓ.ም በቢሾፍቱ ከተማ ከመገናኛ ብዙሃን የስራ ሃላፊዎች እና ጋዜጠኞች ጋር ወይይት በተደረገበት ወቅት ነው።
በውይይት መድረኩ ላይ የመክፈቻ ንግግር ካደረጉት መከካል አንዱ የሆኑት ኮሚሽነር አምባሳደር መሀመድ ድሪር ናቸው።
አምባሳደሩ የምክክር ጉባዔው ሐምሌ 8 ቀን 2018 ዓ.ም እንደሚጀመር አስታውሰዋል።
ጉባዔው የሚካሄደው ደግሞ በ10 መሰረታዊ አጀንዳዎች ላይ ነው ሲሉ አስረድተዋል።

አጀንዳዎቹ ምን ምን እንደሆኑ ወደፊት ለህዝብ እንደሚገለፅ ጠቁመዋል።
ለኢትዮጵያ ይህ ምክክር ምትክ የለውም ፣ ሂደቱ ከምንም ጋር የሚወዳደር አይደለም ያሉት ደግሞ ኮሚሽነር መላኩ ወልደማሪያም ናቸው።
"በኢትዮጵያ ውስጥ ካሉት፣ ወደፊትም ከሚመጡት ፕሮጀክቶች ሁሉ ሀገራዊ ምከክሩ የሚበልጠው የለም" ሲሉ አስረድተዋል።
ይህን እድል አለመጠቀም በታሪክ ሊጸጽትን ይችላል ሲሉም አክለዋል።
እድሉ አንዳያመልጠን መጠቀም አለብን፤ ይህ የመንግስት ጉዳይ፣ የኮሚሽነሮቹ ጉዳይ ሳይሆን የኢትዮጵያ ህዝብ ጉዳይ ነው ብለዋል።
ሐምሌ 8/2018 የሚጀምረውን የሀገራዊ ምክክር ዋና የምክክር መድረክን የመገናኛ ብዙሃን በሀላፊነትና ምክክሩ እንዲሳካ ገንቢ በሆነ መንገድ እንዲዘግቡ በውይይቱ ወቅት ተጠይቋል።
ያሬድ እንዳሻው
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
Website፡ https://www.shegerfm.com/
YouTube : https://shorturl.at/18TS1
Telegram : https://shorturl.at/68aeK
Facebook፡ https://shorturl.at/tm5Q





Comments