top of page

በሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ የተቋቋመው አጣሪ ቡድን በምስራቅ አርሲ ዞን ስላለው ሁኔታ የመጀመሪያ ደረጃ ሪፖርት ይፋ አደረገ፡፡

  • sheger1021fm
  • 1 minute ago
  • 1 min read

ህዳር 1 2018


በኢትዮጵያ የሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ የተቋቋመው አጣሪ ቡድን በምስራቅ አርሲ ዞን ስላለው ሁኔታ የመጀመሪያ ደረጃ ሪፖርት ይፋ አደረገ፡፡


ከየቤተ እምነቱ የተውጣጣው አጣሪ ኮሚቴ ግድያው እምነትን፣ ዘርን፣ ፆታንና እድሜን ያልለየ መሆኑን ማረጋገጡን ተናግሯል፡፡


የማጣራት ስራው የተከወነባቸው በኦሮሚያ ክልል አርሲ ዞን ጉና ወረዳ፣ ሲርካ ወረዳ፣ ቁልቁሉ አቤ ወረዳና መርቲ ወረዳዎች ናቸው ተብሏል፡፡


የአጣሪ ኮሚቴው ዋና ሰብሳቢ መላከ ሰላም ዳዊት ያሬድ በሪፖርታቸው በእነዚህ ወረዳዎች በንጹሃን ሰዎች ላይ በአሰቃቂ ሁኔታ ግድያና እገታ መፈፀሙን ማረጋገጣቸውን ጠቅሰው፤ ከአካባቢው ነዋሪዎች በተገኘው መረጃ የድርጊቱ ፈፃሚዎች በምሽት የሚንቀሳቀሱ ታጣቂ ብድኖች ናቸው ብለዋል፡፡

ree

ኮሚቴው ከሄደባቸው ወረዳዎች መካከል አንዱ በሆነው በአርሲ ዞን ጉና ወረዳ በናኖ ጃዊ ቀበሌ ገበሬ ማህበር በሰዎች ላይ ስለተፈፀመው ግድያና እገታ መፈፀሙን ጠቅሰዋል፡፡


በሽርካ ወረዳም በተመሳሳይ በተለያዩ ቀበሌዎች በንፁሃን ሰዎች ላይ ማሰቃየትና ግድያ ተፈፅሟል፣ ህፃናትን በማገት የቤዛ ክፍያ ተጠይቋ ተብሏል፡፡


የመጀመሪያ ደረጃ ነው፣ ገና የማጣራት ስራው ይቀራል በተባለው በዚህ ሪፖርት ግድያዎች መፈፀማቸውን ከመግለጽ ውጪ በምን ያህል ሰዎች ላይ ግድያው ተፈፀመ የሚለውን አልተነገረም፡፡


የምርመራ ስራው ሲጠናቀቅ ዝርዝር የጥቃቱን ሁኔታ የሚገልፅ ሪፖርት እንደሚያወጣ በኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ አጣሪ ኮሚቴ ተናግሯል፡፡


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

👇👇👇


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page