በ4 ዓመታት በተለያዩ ሀገራት በአስቸጋሪ ሁኔታ ይኖሩ የነበሩ ከ500,000 በላይ ኢትዮጵያዊያን መመለሳቸውን ተነገረ
- sheger1021fm
- 1 day ago
- 1 min read
ህዳር 1 2018
ባለፉት 4 ዓመታት በተለያዩ ሀገራት በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ይኖሩ የነበሩ ከ500,000 በላይ ኢትዮጵያዊያን ወደ ሀገራቸው መመለሳቸውን የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ተናገረ፡፡
ኢትዮጵያዊያኑ በተለያዩ የመካከለኛ ምሥራቅ፣ የአፍሪካ እና እንደ በምይማር ያሉ የእስያ ሀገራት በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ይኖሩ የነበሩ መሆናቸወን ሚኒስቴር መ/ቤቱ ጠቅሷል፡፡
ይህ ሥራ መቀጠሉ የተነገረ ሲሆን በሳውዲ አረቢያ በተለያዩ እስር ቤቶችና ማቆያ ማዕከላት የሚገኙ ሰዎች ከመስከረም 05 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ከ17,000 በላይ ኢትዮጵያዊያን መመለስ ተችላል ተብሏል።

በአሁኑ ወቅትም ከሳውዲ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን የመመለሱ ሥራ ቀጥሏል ሲልም አስረድቷል።
በተመሳሳይ በየመን በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ይኖሩ የነበሩ 36 ሰዎች ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ ተደርጓል የተባለ ሲሆን ሌሎችንም አስፈላጊውን የሰነድ ማጣራት በማድረግ የጉዞ ሰነድ በማዘጋጀት ወደ ሀገራቸው ለመመለስ ከተለያዩ ተቋማት ጋር በመቀናጀት እየተሰራ ነው ሲል የሚኒስቴር መ/ቤቱ መግለጫ አስረድቷል።
በምይማር፣ ላኦስ እና ካምቦዲያ እንዲሁም በሌሎች ሀገራት በተመሳሳይ አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የሚኖሩ ዜጎቻችንን የመመለስ ጥረቱ እንደቀጠለ መሆኑ ተነግሯል።
ሆኖም ግን አሁንም ድረስ ዜጎች በተሳሳተ መረጃ በሕገ ወጥ ደላሎች ተታልለው ወደ ተለያዩ ሀገራት በመጓዝ ለእስራት እና ለሞት እየተዳረጉ በመሆኑ ሰዎች ከህገወጥ ጉዞ ራሳቸውን እንዲከላከሉ እና እንዲጠነቀቁ የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር አሳስቧል።
ወደ ውጪ ሃገራት የሚደረጉ ጉዞዎችና የስራ ቅጥሮች በህጋዊና መንግስት ባስቀመጠው አሰራር ብቻ ሊሆን እንደሚገባ ጨምሮ አሳስቧል።
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
👇👇👇
🌐Website፡ https://www.shegerfm.com/
🎥YouTube https://tinyurl.com/37tux478
🟦Telegram https://t.me/ShegerFMRadio102_1
📘Facebook፡ https://tinyurl.com/4tx8t8wm
💬WhatsApp ፡ https://tinyurl.com/ycxjmm3s












Comments