በ2018 በጀት ዓመት በመንፈቅ ጊዜ 52.26 ቢሊየን ብር ገቢ መሰብሰቡን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ተናገረ።
- sheger1021fm
- 3 hours ago
- 1 min read
ጥር 29/2018
በ2018 በጀት ዓመት በመንፈቅ ጊዜ 52.26 ቢሊየን ብር ገቢ መሰብሰቡን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ተናገረ።
አጠቃላይ ወጪው ደግሞ 52.02 ቢሊዮን ብር መሆኑን አንስቷል።
አገልግሎቱ ከኢነርጂ ሽያጭ፣ ከአዲስ ደንበኛ መስተንግዶ፣ ከማያገለገሉ ንብረቶች ሽያጭና ከልዩ ልዩ ገቢ በጠቅላላው 54.23 ቢሊዮን ብር ለመሰብሰብ ታቅዶ ሲሰራ እንደነበር ተነግሯል።
የተቋሙ የሰበሰበው ገቢ ከእቅዱ 96 በመቶ ያሳካ ነው ተብሏል፡፡

አገልግሎቱ ይህንን ያለው የ2018 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ስድስት ወራት አፈፃፀሙን በተመለከተ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ነው።
በመጀመሪያ ስድስት ወራት ከኢነርጂ ሽያጭ 34.34 ቢሊዮን ብር፣ ከአዲስ ደንበኞች መስተንግዶ 16.7 ቢሊዮን ብር፣ እንዲሁም የማያገለግሉ ንብረቶችን በማስወገድና ከልዩ ልዩ ገቢ 1.2 ቢሊዮን ብር መሰብሰቡን ሲነገር ሰምተናል።
በተጨማሪም በተያዘው በጀት ዓመት 6 ወራት 377,359 አዲስ ደንበኞችን የኤሌክትሪክ አገልግሎት ተጠቃሚ ለማድረግ ታቅዶ፤ 266,916 አባወራ/እማወራዎችን የኤሌክትሪክ አገልግሎት ተጠቃሚ ማድረግ ተችሏል ብሏል የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት።
አፈፃፀሙም ከአምናው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር በ13.2 በመቶ ብልጫ እንዳለው ያነሳው አገልግሎቱ፤ አዲስ ኃይል ከተገናኘላቸው ደንበኞችን መካከል 93.3 ከመቶ የድህረ ክፍያ እንዲሁም 6.7 ከመቶ የቅድመ ክፍያ ቆጣሪ ተጠቃሚ ናቸው ብሏል።
ፋሲካ ሙሉወርቅ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
Website፡ https://www.shegerfm.com/
YouTube : https://shorturl.at/18TS1
Telegram : https://shorturl.at/68aeK
Facebook፡ https://shorturl.at/tm5Q4
WhatsApp : https://shorturl.at/8vwRx
X :- https://x.com/shegerfm?s=2
LinkedIn: https://shorturl.at/Vfe6i
Tiktok : https://shorturl.at/lhYiv
Instagram: https://shorturl.at/9X4S7








