top of page

ሰኔ 17 2017 - የባህር ማዶ ወሬዎች

  • sheger1021fm
  • 8 hours ago
  • 2 min read

እስራኤል ኢራንን በተኩስ አቁም ጣሽነት ከሰሰቻት፡፡

የእስራኤሉ የመከላከያ ሚኒስትር እስራኤል ካትዝ የተኩስ አቁም ከተደረገ በኋላ ኢራን ሚሳየሎች ተኩሳብናለች ማለታቸው አልጀዚራ ፅፏል፡፡

እሳቸውም የእስራኤል ጦር ቴሕራንን እንዲደበድብ ማዘዛቸው ተሰምቷል፡፡

እስራኤል እና ኢራን ላለፉት 12 ቀናት አንዷ በሌላዋ ላይ ጥቃት ሲፈፅሙ መቆየታቸውን መረጃው አስታውሷል፡፡

እስራኤል በኢራን በፈፀመችው ድብደባ ከ400 በላይ ሰዎች መገደላቸው ይነገራል፡፡

ኢራን በእስራኤል ላይ በፈፀመችው ድብደባ ከ25 የማያንሱ ሰዎች ተገድለዋል ተብሏል፡፡

ገና ከማለዳው እየተጣሰ ነው የተባለው የተኩስ አቁም ቀጣይ እጣ ፈንታው ምን እንደሚሆን አልታወቀም፡፡

በተያያዘም እስራኤል ኢራንን በተኩስ አቁም ጣሽነት ከሰሰቻት፡፡

የእስራኤሉ የመከላከያ ሚኒስትር እስራኤል ካትዝ የተኩስ አቁም ከተደረገ በኋላ ኢራን ሚሳየሎች ተኩሳብናለች ማለታቸው አልጀዚራ ፅፏል፡፡

እሳቸውም የእስራኤል ጦር ቴሕራንን እንዲደበድብ ማዘዛቸው ተሰምቷል፡፡

እስራኤል እና ኢራን ላለፉት 12 ቀናት አንዷ በሌላዋ ላይ ጥቃት ሲፈፅሙ መቆየታቸውን መረጃው አስታውሷል፡፡

እስራኤል በኢራን በፈፀመችው ድብደባ ከ400 በላይ ሰዎች መገደላቸው ይነገራል፡፡

ኢራን በእስራኤል ላይ በፈፀመችው ድብደባ ከ25 የማያንሱ ሰዎች ተገድለዋል ተብሏል፡፡

ገና ከማለዳው እየተጣሰ ነው የተባለው የተኩስ አቁም ቀጣይ እጣ ፈንታው ምን እንደሚሆን አልታወቀም፡፡

በኬንያዋ ርዕሰ ከተማ ናይሮቢ በእስር ቤት እንዳለ ሕይወቱ አልፎ በተገኘው ወጣት መምህር እና የድረ ገፅ መጣጥፍ አቅራቢ አልበርት ኦጅዋንግ ግድያ የተጠረጠሩ 3 የፖሊስ መኮንኖች ክስ ተመሰረተባቸው፡፡

ወጣቱ በፖሊስ ጣቢያ እስር ቤት እያለ ሕይወቱ ማለፉ በአገሪቱ ከፍተኛ ምሬት እና ቁጣ ቀስቀሶ መሰንበቱን ታይምሰ ላይቭ አስታውሷል፡፡

ቀደም ሲል ፖሊስ የወጣቱ ሕይወት ያለፈው ራሱን ከእስር ቤት ክፍሉ ግድግዳ ጋር በማጋጨቱ ነው የሚል መግለጫ አውጥቶ ነበር፡፡

የአስከሬን ምርመራው ቀዳሚ ግኝት ግን ኦጅዋንግ ከመሞቱ አስቀድሞ ድብደባ እንደተፈፀመበት የሚያሳይ ነው ተብሏል፡፡

በዚህም የተነሳ ተቆጥተው ለአደባባይ ሰልፍ የወጡ ኬኒያውያን የፖሊስ ሹሞች ከሀላፊነት ተነስተው እንዲጠየቁ ሲወተውቱ ሰንብተዋል፡፡

ወጣቱን ስሜን አጥፍቷል ብለው ያሳሰሩት የፖሊስ ምክትል አዛዡ ባለፈው ሳምንት ከሀላፊነት መገለላቸው ለትውስታ ተጠቅሷል፡፡

የግሪክ ፖሊስ ለኢራን ሲሰልል ደርሼበታለሁ ያለውን ተጠርጣሪ መያዙን እወቁልኝ አለ፡፡

በኢራን ሰላይነት ተጠርጥሮ የተያዘው ግለሰብ በዜግነት አዘርባጃናዊ ነው መባሉን አልጀዚራ ፅፏል፡፡

እንደሚባለው ግለሰቡ በግሪክ ክሬት ደሴት የሚገኘውን የሰሜን አትላንቲክ የጦር ቃል ኪዳን ድርጅት /ኔቶን/ የጦር ሰፈር ሲቃኝ በሰላይነት ተጠርጥሮ ተይዟል፡፡

ጥብቅ ስፍራዎችንም ፎቶ ግራፍ ሲያነሳ እንደነበር ተጠቅሷል፡፡

ከግለሰቡ ላይ ከ5 ሺህ በላይ ፎቶ ግራፎች እና በጣም ብዙ የቪዲዮ ምስሎችም እንደተያዙበት ተጠቅሷል፡፡

በቆጵሮስም ቀደም ሲል ተመሳሳይ ስምሪት የነበረው ሌላ ግለሰብም እንደተያዘ መረጃው አስታውሷል፡፡

የኔነህ ከበደ

የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

コメント

Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page