top of page

ኢትዮጵያ የባህር በር በሰላማዊ መንገድ እንድታገኝ ቱርክዬ በዲፕሎማሲያዊ መንገድ ጫና እንድታደርግ ከቱርክዬ ፕሬዚዳንት ጋር ጠንከር ያለ ውይይት ማድረጋቸውን ጠ/ሚ ዐቢይ ተናገሩ።

  • 19 hours ago
  • 1 min read

የካቲት 11/2018


ኢትዮጵያ የባህር በር በሰላማዊ መንገድ እንድታገኝ ቱርክዬ በዲፕሎማሲያዊ መንገድ ጫና እንድታደርግ ከቱርኩ ፕሬዚዳንት ጋር ጠንከር ያለ ውይይት ማድረጋቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ተናገሩ።


ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህን ያሉት ከቱርኩ ፕሬዚዳንት ሪሲፕ ታይፕ ኤርዶዋን ጋር ሆነው በቤተመንግስት መግለጫ በሰጡበት ወቅት ነው።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በንግግራቸው ኢትዮጵያ የባህር በር በሰላማዊ መንገድ ማግኘት የምትችልበት ሁኔታ ለይ ቱርክዬ በዲፕሎማሲያዊ መስኩ ጫና በመፍጠር እንዲያግዙ ከፕሬዝዳንት ኤርዶዋን ጋር ተወያይተናል ብለዋል።


ፕሬዚዳንት ኤርዶዋን ከዚህ አንፃር የበኩላቸውን ሚና እንዲጫወቱ ጠንከር ያለ ውይይት አደርገናል፣ ለዚህም ምስጋና አቀርባለሁ ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ።


ከዚህ በተጨማሪም በኢትዮጵያ እና በቱርክዬ መካከል ያለው ዓመታዊ የንግድ ልወውጥ ቢያንስ አንድ ቢሊዮን ዶላር እንዲሞላ በሁለቱም ሀገራት ታስቦበት እንዲሰራ ከስምምነት መደረሱን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጠቅሰዋል።

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page