top of page

ምርቶች በወጣላቸው ደረጃ መሰረት ተዘጋጅተው ለገበያ መዋላቸውን ለማረጋገጥ የሚደረገው የቁጥጥር የላላ ሆኖ ቀጥሏል፡፡

  • sheger1021fm
  • Nov 10, 2025
  • 1 min read

ህዳር 1 2018


ምርቶች በወጣላቸው ደረጃ መሰረት ተዘጋጅተው ለገበያ መዋላቸውን ለማረጋገጥ የሚደረገው የቁጥጥር የላላ ሆኖ ቀጥሏል፡፡


መረጃዎችን የሚያጸድቀው ቦርድ የሚወጡ ደረጃዎችን አተገባበር በየጊዜው እንዲከታተል የሚያስችል አዲስ አሰራር ሊከተል እንደሆነም ሠምተናል፡፡


በሌላ በኩል ለሁለት ተጨማሪ ሀገር በቀል ምግብ ነክ ምርቶች በኢትዮጵያ የደረጃዎች ኢንስቲትዩት ደረጃ መዘጋጀቱ ተነግሯል፡፡


የኢትዮጵያ የደረጃዎች ኢንስቲትዩት ምግብ ነክ ለሆኑ ስድስት አገር በቀል ምርቶች ደረጃ ማዘጋጀቱ ይታወሳል፡፡


ሽሮ፣ በርበሬ፣ ቆሎ፣ በሶ፣ አረቄ እና ጠጅ ደረጃው የተዘጋጀላቸው ምርቶች ናቸው፡፡


ለምርቶቹ የወጣውን ደረጃ ህብረተሰቡ እንዲያውቀው እንዲሁም የተመረጡ የጥቃቅን እና አነስተኛ ተቋማት ደረጃውን መሰረት አድርገው ምርቱን እንዲያዘጋጁ መደረጉን በኢንስቲትዩቱ የደረጃ ዝግጅት መሪ ስራ አስፈጻሚ አቶ ይልማ መንግስቱ ነግረውናል፡፡

ኢንስቲትዩቱ ለተጨማሪ አገር በቀል ምግብ ነክ ምርቶች ደረጃ እንዲያዘጋጅ ጥያቄ እየቀረበለት ነውም ብለውናል፡፡


ጥያቄውን መሰረት በማድረግ ለጮኮ እና አንጮቴ ደረጃ መዘጋጀቱን ነግረውናል ሌሎቹ ደግሞ በሂደት ላይ ናቸው ብለዋል፡፡


የአኗኗር ዘይቤ እየተቀረ በመምጣቱ ብዙ ሰዎች የተዘጋጁ ምርቶችን ገዝተው መጠቀም ይመርጣሉ የሚሉት አቶ ይልማ ፤

እነዚህ ለንግድ ዓላማ የሚውሉ ምርቶች ጥራታቸው ተጠብቆ እንዲሸጡ ሲባል ደረጃውን ማዘጋጀት አስፈላጊ ሆኗል ብለዋል፡፡


ምርቶች በወጣላቸው ደረጃ መሰረት ተመርተው ለህብረሰቡ መቅረባቸውን ለማረጋገጥ የሚደረገው የቁጥጥር ስራ ላይ ግን አሁንም ችግር እንዳለ አቶ ይልማ ተናግረዋል፡፡


ይሄ ምግብ ነክ ሆኑ አገር በቀል ምርቶች ላይ ብቻ ሳይሆን በሌሎቹም ላይ ያለ ችግር ነው ብለዋል፡፡


የኢትዮጵያ የደረጃዎች ኢንስቲትዩት ምግብ ነክ ለሆኑ አገር በቀል ምርቶች ደረጃ የሚያዘጋጀው የኢትዮጵያ ሕብረተሠብ ጤና ኢንስቲትዩት የሚያካሂደውን ጥናት መሰረት አድርጎ ነው ተብሏል፡፡


ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ…..

ንጋቱ ረጋሳ


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

👇👇👇


Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page