top of page

ሚያዝያ 28፣2016 - ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በመጪዎቹ ሶስት ዓመታት 1.5 ቢሊዮን ዶላር ሙዓለ ነዋይ ፈሰሰ ለማድረግ ማቀዱን ተናገረ

ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በመጪዎች ሶስት ዓመታት 1.5 ቢሊዮን ዶላር ሙዓለ ነዋይ ፈሰሰ ለማድረግ ማቀዱን ተናገረ።


በዚህም 5 ሺህ የቴሌኮም ማማዎች እንደሚገነባ ኩባንያው ለሸገር በላከው መግለጫ ላይ ጠቅሷል።


በሚቀጥሉት ሦስት ዓመታት ውስጥ 5 ሺህ አዳዲስ የኔትወርክ ማማዎችን ሲዘረጉ አጠቃላይ የማማዎች ቁጥር 7 ሺህ እንደሚደርስ ኩባንያው ተናግሯል፡፡


በአሁኑ ጊዜ ኩባንያው አገልግሎት ከሚሰጥባቸው 2500 የቴሌኮም ማማዎች ውስጥ 1500 ራሱ የገነባናቸው መሆናቸውንም አስረድቷል።

የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ዊም ቫንሄለፑት ኔትወርክን ለማስፋፋት እና ለመላው ኢትዮጵያዊያን የቴሌኮም ትስስርን ለማሻሻል ከፍተኛ ጥረት እያደረግን ነው ብለዋል።


ሳፉሪኮም ኔትወርክ ማስፋፋት ላይ የሚያደርገው ኢንቬስትመንት የዲጂታል ትራንስፎርሜሽኑን ግብ እውን ለማድረግ እና የኢኮኖሚ እድገትን ለማገዝ ያለንን ከፍተኛ አቋም ያሳያል ሲሉም ስራ አስፈፃሚው አስረድተዋል።


ኩባንያው በኔትወርክ እና አገልግሎቱን ለማስፋፋት በሚያርገው ጥረት የኮሙኒኬሽን ባለሥልጣን ትብብር እንዳይለየው ጠይቋል።


ንጋቱ ሙሉ


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…





bottom of page