top of page

ሚያዝያ 24፣2016 ''አንድ ኢትዮጵያዊ በዓመት የሚመገበው ስጋ 7.5 ኪ.ግራም ነው''

በፋሲካ፣ በትንሳኤ በዓል ዋዜማ ላይ ሆነን የበግ ዋጋ ስንጠይቅ 10 ሺህ ፣ 12 ሺህ እና 15 ሺህ የሚል መልስ እናገኛለን፡፡


መጠኑን በኪሎ አድርገን የቄራዎች ድርጅት የሚሸጥበትን ዋጋ ስንመለከት 1 ኪሎ የበግ ስጋ ዋጋ 500 ብር ይሸጣል፡፡


በሌላ በኩል ኢትዮጵያ በቁም እንስሳት ሀብቷ ከቀዳሚዎች የአለም ሀገራት ተርታ እንደምትሰለፍ ይነገራል፡፡


የበግ እና ፍየሎችን ብቻ ለይተን ብናይ እንኳ በኢትዮጵያ 90 ሚሊዮን በግ እና ፍየል አላት ይባላል፡፡


የኢትዮጵያ ስርዓት ምግብ ሰነድ ላይ እንደተጠቀሰው አንድ ኢትዮጵያዊ በዓመት የሚመገበው ስጋ 7.5 ኪ.ግራም ነው፡፡


ይህም ከሰሃራ በስተደቡብ ካሉ ሀገሮች ጋር እንኳን ሲነፃፀር በጣም ዝቅተኛ ነው፡፡


እውነት 90 ሚሊዮን በግ እና ፍየል ኢትዮጵያ አላት ወይ?


ካለትስ የበግ እና ፍየል ዋጋ ውድም ብርቅም ለምን ሆነ?


ጥያቄውን ለፕሮፌሰር ብርሃኑ በላይ አቅርበንላቸዋል፡፡


ፕሮፌሰር ብርሃኑ በሞያቸው የእንስሳት ሀብት ተመራማሪ ሲሆኑ ለ35 አመት በዘርፉ ላይ ሰርተዋል፡፡


በአሁኑ ሰዓትም በአለም አቀፍ የደረቃማ አካባቢዎች የግብርና ምርምር ማዕከል ውስጥ ይሰራሉ ፡፡



የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…





bottom of page