top of page

ሚያዝያ  16፣2016 - በሰሜን ተራሮች ብሄራዊ ፓርክ ላይ የተነሳው እሳት ሙሉ ለሙሉ መጥፋቱ ተነግሯል

ሚያዝያ 10/ 2016 በሰሜን ተራሮች ብሄራዊ ፓርክ ላይ የተነሳው እሳት ሙሉ ለሙሉ መጥፋቱ ተነግሯል።

 

በተለያዩ አካላት ርብርብ እሳቱን ከትናንት በስትያ ምሽት ላይ መቆጣጠር እንደተቻለ የነገሩን የሰሜን ተራሮች ብሄራዊ ፓርክ ፅህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ኤፍሬም ወንድዬ ናቸው።

 

በፓርኩ ውስጥ ባለው ተቀጣጣይ ክምችት ተዳፍኖ የቀረ እሳት ካለ በሚል የአሰሳ ስራ እየተሰራ ይገኛልም ብለዋል።

ስለ እሳቱ መነሻ ምክንያት ለማወቅ ማጣራት እየተካሄደ ነው ያሉን አቶ ኤፍሬም ከዚሁ ጋር በተገናኘ ተጠረጥረው የተያዙ ሰዎች ግን እንዳሉ ነግረውናል፡፡

 

ፓርኩን ህብረተሰቡ በእኔነት ስሜት እንዲጠብቀው በማድረግ ዘላቂ የሆነ የእሳት መከላከል ስራ እንሰራለን የሚሉት ሃላፊው፤ ጥያቄ እያስነሱብን ላሉ የዝግጅት ስራዎችም ምላሽ መስጠት እንዳለብን ተረድተናል ብለዋል።

 

የሰሜን ተራሮች ብሄራዊ ፓርክ 412 ስኩዌር ኪሎ ሜትር ስፋት ያለው ሲሆን እንደ ዋልያ፣ ቀይ ቀበሮ እና ጭላዳ ዝንጀሮ ያሉ ብርቅዬ የዱር እንስሳት መገኛ መሆኑ ተነግሯል።

 

ንጋቱ ረጋሣ


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

 

Telegram:  @ShegerFMRadio102_1

 

 

 

 

 

bottom of page