top of page

መጋቢት 4፣2016 - የአውሮፓ ህብረት፤ መንግስት የንግድ ስርአቱን ለማዘመን ለቀረፀው ፕሮግራም አዲስ የድጋፍ ማዕቀፍ ማዘጋጀቱን ተናገረ

  • Mar 13, 2024
  • 1 min read

የኢትዮጵያ መንግስት የንግድ ስርአቱን ለማዘመን ለቀረፀው ፕሮግራም አዲስ የድጋፍ ማዕቀፍ ማዘጋጀቱን የአውሮፓ ህብረት ተናገረ።


የአውሮፓ ህብረት የኢትዮጵያን የግል ዘርፍ እና የንግድ ስርአት ለመደገፍ ታስበው የተዘጋጁ መርሃ ግብሮችን ስራ ላይ እዋለ እንደሚገኝ ተናግሯል።


ከተወሰኑ ዓመታት ወዲህ ደግሞ ትኩረቱ የኢትዮጵያ መንግስት የንግድ ስርአቱን ለማዘመን በቀረፀው ፕሮግራም ላይ ማድረጉን፤ በኢትዮጵያ የአውሮፓ ህብረት ፅህፈት ቤት የፕሮግራም አስተባባሪ አቶ ልዑል ሃብቴ ነግረውናል፡፡


በኢትዮጵያ የግሉ ዘርፍ ሚና በኢኮኖሚው ውስጥ እንዲያድግ ህብረቱ ሶስት ፕሮጀክቶችን ቀርፆ እየሰራ እንደሚገኝም ሠምተናል፡፡


ሶስቱ ፕሮጀክቶች በአጠቃላይ ወደ አስር ሚሊየን ዩሮ በጀት በህብረቱ እንደተያዘላቸው አቶ ልዑል ተናግርዋል፡፡


ህብረቱ ከገንዘብ ድጋፍ ባሻገር ሞያዊ ዕገዛም እንደሚያደርግ አስተባባሪው ተናግረዋል።



ንጋቱ ረጋሣ



የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…



Recent Posts

See All
የቤት ገዢዎችን የመግዛት አቅም ለማበርታት እንዲያግዝ ፖሊሲ የተዘጋጀለት የሞርጌጅ ባንክ እንዲቋቋም ተጠየቀ።

ሚያዝያ 20/2018 የቤት ገዢዎችን የመግዛት አቅም ለማበርታት እንዲያግዝ ፖሊሲ የተዘጋጀለት የሞርጌጅ ባንክ እንዲቋቋም ተጠየቀ። በኢትዮጵያ ያለው የግለሰቦች ቤት የመግዛት አቅም ከጊዜ ጊዜ እየቀነሰ መምጣት፣የብርየመግዛት አቅም መዳከም የግለሰቦች ቤት የመግዛት አቅም አብሮ ተዳክሟል ይላሉ የሪል እስቴት

 
 
 

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page