top of page

መጋቢት 25፣2016 - የወጪ ንግድ ገቢ ከአምናው ጋር ሲመሳከር የ164 ሚሊዮን ዶላር ቅናሽ አሳይቷል  ተባለ

  • Apr 3, 2024
  • 1 min read

ኢትዮጵያ ባለፉት 8 ወራት ከወጪ ንግድ ያገኘችው ገቢ ከአምናው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲመሳከር የ164 ሚሊዮን ዶላር ቅናሽ አሳይቷል  ተባለ፡፡

 

በጊዜው ከወጪ ንግድ ለማግኘት የተቻለው የእቅዱን 69 በመቶ ብቻ ነው ተብሏል፡፡

 

የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር የ8 ወር የስራ ክንውን ሪፖርት ለሕዝብ እንደራሴዎች  ምክር ቤት አቅርቧል፡፡

 

ሪፖርቱን በንባብ ለእንደራሴዎቹ ያቀረቡት የንግድ ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ሚኒስትር ገብረ መስቀል ጫላ ናቸው፡፡

 

ሚኒስትሩ በሪፖርታቸው በ 8 ወር ዉስጥ ከወጪ ንግድ 3.14 ቢሊዮን ዶላር  ለማግኘት ታቅዶ ማግኝት የተቻለዉ ግን 2.16 ቢሊዮን ዶላር ነው ተብሏል፡፡

 

ከባለፈው አመት የ8 ወር የስራ አፈፃፀም 2.3 ቢሊየን ዶላር ተገኝቶ ነበር ዘንድሮ ግን በ8 ወር ውስጥ ማግኘት የተቻለው 2.1 ቢሊየን ዶላር ነው ተብሏል፡፡

የዘንድሮ አመት የ8 ወር የስራ አፈፃፀም ከአምናው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲመሳከር የ164 ሚሊዮን ዶላር ቅናሽ እንዳለው የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ሚኒስትር ገ/መስቀል ጫላ አስረድተዋል፡፡

በዚህም ድርሻቸው ግብርና 73.1 ማኒፋክቸሪንግ 50.9 በመቶ ማዕድን 53.9 በመቶ እና ኤሌክትሪክ 69 በመቶ ድርሻ አላቸው ተብሏል፡፡

ሚኒስትሩ በሪፖርታቸው በርካታ ችግሮች ቢኖሩም የበረቱት ግን የህግ ወጥ ንግድና የሰላም እጦት እንደሆነ አብራርቷል፡፡

 

የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር በበጀት አመቱ አዳዲስ የገበያ መዳረሻዎችን አግኝቻለሁ ማለቱን ሰምተናል፡፡

 

ከዚህ በፊት ወደ ሳውዲ አረቢያ ለ3 ዓመታት ተቋርጦ የቆየው የቁም እንስሳት ግብይትም በበጀት አመቱ ተጀምሯል ብሏል፡፡

 

ያሬድ እንዳሻው

 

የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

 

 

 

ShegerFM: @ShegerFMRadio102_1

 

Recent Posts

See All
ዘንድሮ በአዲስ አበባ የ8ኛ ክፍል ተማሪዎች ከተማ አቀፍ ፈተና ካስፈተኑ ትምህርት ቤቶች 66 በመቶዎቹ ተማሪዎቻቸው ሙሉ በሙሉ የማለፊያ ነጥብ አምጥተዋል፡፡

ሰኔ 22/2018 ዘንድሮ በአዲስ አበባ የ8ኛ ክፍል ተማሪዎች ከተማ አቀፍ ፈተና ካስፈተኑ ትምህርት ቤቶች 66 በመቶዎቹ ተማሪዎቻቸው ሙሉ በሙሉ የማለፊያ ነጥብ አምጥተዋል፡፡ የከተማዋ ትምህርት ቢሮ በሰጠው መግለጫ ከመንግስት ትምህርት ቤቶች ተማሪዎች 95 ነጥብ 8 በመቶ፤ ከግል ት/ቤት ተማሪዎች ደግሞ ከ99

 
 
 

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page