top of page

ግንቦት 24/2018 ዓ.ም በተደረገው ሀገራዊ ምርጫ 75 የግል እጩዎች ተወዳድረው 18ቱ አሸንፈዋል።

  • 2 hours ago
  • 2 min read

ሰኔ 22/2018


ግንቦት 24/2018 ዓ.ም በተደረገው ሀገራዊ ምርጫ 75 የግል እጩዎች ተወዳድረው 18ቱ አሸንፈዋል።



8ቱ የህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት መቀመጫ ያገኙ ሲሆን ቀሪዎቹ አስሩ የክልል ምክር ቤት መቀመጫ ያገኙ ናቸው።


አሸናፊዎቹ ግን ከተሳትፎ በዘለለ ምን ማድረግ ይችላሉ?


ለመሆኑ እነዚህ አሸናፊ የግል እጩዎች ከተሳትፎ በዘለለ ፓለቲካዊ ለውጥ የማምጣት አቅም አላቸው ወይ? ከመካከላቸው ሁለቱን አነጋግረናል፡፡


በጉዳዩ ዙሪያ የፖለቲካ ባለሙያ ሃሳብም ጠይቀንበታል፡፡


አቶ ቀጀላ መርዳሳ ለረጅም ጊዜ በኦሮሞ ነጻነት ግንባር ፓርቲ አመራርነታቸው ይታወቃሉ፡፡ ከ2014 ዓ.ም መጀመሪያ እስከ 2016 ዓ.ም መጨረሻ ድረስ የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ሆነው አገልግለዋል፡፡



አሁንም ቢሆን በፓርቲው ያለኝ የአመራርነትና የአባልነት ቦታ እንዳለ ነው፤ በግል ለመወዳደር የተገደድኩት በፓርቲው ሊቀመንበር ያለ አግባብ እጩ ሆኜ እንዳልቀርብ በመደረጌ ነው ብለውናል፡፡


የፓርቲያቸው ኦነግ መተዳደሪያ አባልነትን ሳይለቁ በግል መወዳደርን ስለማይከለክል ነው ወደ ውድድሩ የገባነው፤ በ2019 ዓ.ም በሚጀምረው የፓርላማ ቆይታቸውም ኦነግ የሚያራምደውን አቋም እንደሚያንፀባርቁና የተመረጡበትን የአምቦ አካባቢ ህዝብ ጥያቄዎችን በማንሳት ድምጽ እንደሚሆኑ ጠቁመዋል፡፡


በዘንድሮ ምርጫ ለህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት ካሸነፉ 8 የግል ተወዳዳሪዎች መካከል ኡዝታዝ ካሚል ሸምሱ ሌላኛው ናቸው፡፡


ከዚህ ቀደም በነበረው 6ተኛው ሃገራዊ ምርጫም እንዲሁ በግል ተወዳድረው በማሸነፍ የፓርላማ አባል መሆናቸውን ያስታወሱት ኡዝታዝ ካሚል ሸምሱ በአንድ ፓርቲ ከምገደብ በግሌ ብወዳደር በተሻለ መንገድ የመረጠኝን ማህበረሰብ አገለግላለሁ ብለዋል፡፡



የፓርላማ አባልነታቸውን በመጠቀም በአባይ ጉዳይ ላይ ግብፆች ለሚያነሱዋቸው ጥያቄዎች በተለይ በአረብኛ ቋንቋ በአለም አቀፍ ሚዲያዎች የኢትዮጵያን አቋም ሲያንፀባርቁ መቆየታቸውን የሚያነሱት ኡዝታዝ ካሚል ከዚህ በኋላ ደግሞ በባህር በር ጉዳይ ላይ ሃገር ያላትን አቋም ለማስረዳረትና ለመሟገት እንደሚሰሩ እንዲሁም፤ በሚቀጥለው የፓርላማ ቆይታቸውም እንደ አቶ ቀጀላ ሁሉ ቀዳሚው ትኩረታቸው በሃገሪቱ ሰላም እንዲሰፍን በውክልናቸው የበኩላቸውን መወጣት ሲሆን በሌሎችም ኢኮኖሚያዊ ናማህበራዊ ጉዳዮች የማህበረሰቡ ድምጽ ለመሆን መሰናዳታቸውን ነግረውናል፡፡


በፓርላማ ቆታችሁ ከተሳትፎ በዘለለ የሚፈለገውን ፓለቲካዊ ለውጥ ለማምጣት አቅማችሁና ተሳትፏችሁ ከፓርቲዎች አንፃር ውስን አይሆንም ወይ? ያልናቸው የግል ተወዳዳሪዎቹ፤ ለውጥ ለማምጣት በፓርቲም ይሁን በግል መሳተፍ እኩል ነው፤ እንደውም ቁጥራችን አንዳንድ ፓርቲዎች ካሸነፉት ወንበር የበለጠ ነው፤ የሚል ምላሽ ሰጥተውናል፡፡


በጉዳዩ ዙሪያ ሀሳባቸውን የሰጡን የፖለቲካ ተንታኙ ዶክተር ጌትዬ ትርፌ ግን በዚህ ሃሳብ አይስማሙም፤

አሁን ባለው የምክር ቤቱ አሰራር በተለይ የስራ አስፈጻሚው አካል ግምገማና ሪፖርት ስብሰባ እንኳን ሃሳባቸውን ለመግለጽ እድል የሚሰጠው አብላጫውን ወንበር ለያዘው ፓርቲ ነው፤


በመቀጠል ጥቂት ድምጽ ይዘው ለገቡ ፓርቲዎች ነው፤የግል እጩዎች እድል አያገኙም፤ቢያገኙም እንኳን አልፎ አልፎ ነው፤የመናገር እድል በሌለበት ለውጥ ሊያመጡ አይችሉም ብለውናል፡፡


እጩዎቹ ይዘዋቸው የሚመጡትን የህዝብ ጥያቄዎች ማስተጋባትና ለውጥ ማምጣት የሚችሉት እየተካሄደ ባለው ሃገራዊ ምክክር በሚወሰኑ ውሳኔዎች የየምክር ቤቶቹ የውስጥ አሰራሮች ላይ ለውጥ ከተደረገ እንደሆነም ዶክተር ጌትዬ ያነሳሉ፡፡


በዘንድሮው ምርጫ ካለፈው ምርጫ ቁጥራቸው በእጥፍ የጨመረ የግል እጩዎች ወደ ፓርላማው ይገባሉ ተብሎ ይጠበቃል፤ተሳትፏቸው እንዲበረታና ያሰቡንትን እንዲያሳኩ ካስፈለገ በሃገራዊ ምክክሩ የምክር ቤቶቹን አሰራር ለመቀየር የሚያስችሉ ውሳኔዎች እንደሚያስፈልጉ ተጠቁሟል፡፡


ሙሉ ዘገባውን ለማድመጥ.....


ምንታምር ጸጋው

Recent Posts

See All
ዘንድሮ በአዲስ አበባ የ8ኛ ክፍል ተማሪዎች ከተማ አቀፍ ፈተና ካስፈተኑ ትምህርት ቤቶች 66 በመቶዎቹ ተማሪዎቻቸው ሙሉ በሙሉ የማለፊያ ነጥብ አምጥተዋል፡፡

ሰኔ 22/2018 ዘንድሮ በአዲስ አበባ የ8ኛ ክፍል ተማሪዎች ከተማ አቀፍ ፈተና ካስፈተኑ ትምህርት ቤቶች 66 በመቶዎቹ ተማሪዎቻቸው ሙሉ በሙሉ የማለፊያ ነጥብ አምጥተዋል፡፡ የከተማዋ ትምህርት ቢሮ በሰጠው መግለጫ ከመንግስት ትምህርት ቤቶች ተማሪዎች 95 ነጥብ 8 በመቶ፤ ከግል ት/ቤት ተማሪዎች ደግሞ ከ99

 
 
 

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page