top of page

ኢትዮጵያ ከዩሮ ቦንድ አበዳሪዎች ያለባትን እዳ ለማሸጋሸግ ከአበዳሪዎቹ ጋር ስምምነት ላይ መድረሷ ተነግሯል፡፡

  • 35 minutes ago
  • 1 min read

ሰኔ 22/2018


ኢትዮጵያ ከዩሮ ቦንድ አበዳሪዎች ያለባትን እዳ ለማሸጋሸግ ከአበዳሪዎቹ ጋር ስምምነት ላይ መድረሷ ተነግሯል፡፡


የ1 ቢሊዮን ዶላር እዳዋን ለማሸጋሸግ ከአበዳሪዎቹ ጋር ያደረገችው ተደጋጋሚ ድርድር ውጤት ሳያመጣ መቆየቱ ይታወሳል፡፡ እንዲያውም አበዳሪዎቹ ጉዳዩን ወደ ህግ እንወስደዋለን እያሉም እንደነበር አይዘነጋም፡፡


ከገንዘብ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ እንደሚያሳየው ከሰኔ አምስት እስከ 28 ቀን 2026 በተደረገው ዝግ ውይይት የእዳ ሽግሽግ ድርድሩ በመርህ ደረጃ የሰመረ ሆኗል፡፡



በዚህም መሰረት ከ2 አመት በፊት መክፈል ከነበረበት የ1 ቢሊዮን ዶላር እዳ ላይ አበዳሪዎቹ 12 በመቶውን ለመቀነስ ተስማምተዋል፡፡


በዚህም ዋናው እዳ ከ1 ቢሊዮን ዶላር ወደ 880 ሚሊዮን ዶላር ዝቅ እንዲል ስምምነት ላይ ተደርሷል፡፡


በሌላ በኩል በፈረንጆቹ አቆጣጠር በ2024 ተከፍሎ ማለቅ የነበረበት ከ99 ሚሊዮን ዶላር በላይ ወለድም ስምምነቱ ህጋዊ ሆኖ ሲያልቅ በአንድ ጊዜ እንዲከፈል አበዳሪዎቹና ኢትዮጵያ መስማማታቸው ታውቋል፡፡


የአከፋፈል ሁኔታውን በተመለከተም ዋናው እዳ በ4 አመት ውስጥ እ.ኤ.አ እስከ መጭው ሐምሌ 15,2029 ተከፍሎ ያልቃል ተብሏል ፡፡


ኢትዮጵያ ከዩሮ ቦንድ አበዳሪዎች የወሰደችው የ1 ቢሊዮን ዶላር እዳ የኢንዱስትሪ ፓርኮችን ለመገንባት ወስዳው የነበረ መሆኑ ይታወሳል፡፡


የነበረባትን እዳ ለማሸጋሸግ ኢትዮጵያ ከተለያዩ አበዳሪዎቿ ጋር ያደረገችው ድርድር ሰምሮ የቀረው የዩሮ ቦንድ አበዳሪዎች እዳ እንደነበር አይዘነጋም፡፡


በመርህ ደረጃ እዳው እንዲሸጋሸግ ስምምነት ላይ በመድረሱም ኢትዮጵያ የተለያዩ ጥቅሞችን አግኝታለች፡፡

ከዋናው እዳ ላይ 120 ሚሊዮን ዶላር ተቀንሶላታል፡፡


በአንዴ መክፈል የነበረባትን ዋናውን እዳ በ4 አመት የጊዜ ማዕቀፍ በሂደት እንድትከፍል ተፈቅዶላታል፡፡


በዚህ መሰረት እስከ ሐምሌ 15,2026 ድረስ 180 ሚሊዮን ዶላር ሌላ 100 ሚሊዮን ዶላር ደግሞ በመጭው አመት ሐምሌ 15፣2027 እንድትከፍል ተስማምተዋል፡፡ እንዲሁም 300 ሚሊዮን ዶላር ሐምሌ 15,2028 እና ቀረውን 300 ሚሊዮን ዶላር ደግሞ ሀምሌ 15,2029 እንድትክፈል በመርህ ደረጃ ስምምነት ላይ ተደርሷል፡፡


ስምምነቱንም IMFን ጨምሮ አለም አቀፍ አበዳሪዎች አልነቀፉትም ተብሏል፡፡


ትዕግሥት ዘሪሁን



Recent Posts

See All
ዘንድሮ በአዲስ አበባ የ8ኛ ክፍል ተማሪዎች ከተማ አቀፍ ፈተና ካስፈተኑ ትምህርት ቤቶች 66 በመቶዎቹ ተማሪዎቻቸው ሙሉ በሙሉ የማለፊያ ነጥብ አምጥተዋል፡፡

ሰኔ 22/2018 ዘንድሮ በአዲስ አበባ የ8ኛ ክፍል ተማሪዎች ከተማ አቀፍ ፈተና ካስፈተኑ ትምህርት ቤቶች 66 በመቶዎቹ ተማሪዎቻቸው ሙሉ በሙሉ የማለፊያ ነጥብ አምጥተዋል፡፡ የከተማዋ ትምህርት ቢሮ በሰጠው መግለጫ ከመንግስት ትምህርት ቤቶች ተማሪዎች 95 ነጥብ 8 በመቶ፤ ከግል ት/ቤት ተማሪዎች ደግሞ ከ99

 
 
 

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page