መጋቢት 17/2018 - የኔዘርላንድ ኢንስቲትዩት ፎር መልቲ ፓርቲ በመጪው ምርጫ የሚሳተፉ 80 ሴት እጩዎችን በመያዝ ውይይት ማድረጉ ተሰማ፡፡
- 2 hours ago
- 1 min read
መጋቢት 17/2018
የተለያዩ ሀሳቦችን በመያዝ በፖለቲካ ውስጥ የሚሳተፉ ሰዎች ከእርስ በእርስ ጥላቻ እና ካልተገባ መጠላለፍ ወጥተው በጋራ እንዲነጋገሩ እና በሀሳብ የበላይነት እንዲያምኑ እየሰራሁ ነው ያለው የኔዘርላንድ ኢንስቲትዩት ፎር መልቲ ፓርቲ በመጪው ምርጫ የሚሳተፉ 80 ሴት እጩዎችን በመያዝ ውይይት ማድረጉ ተሰማ፡፡
የኢትዮጵያ ባለዕራይ መሪዎች ማህበር ስራ አስፈፃሚ አካል ወ/ሪት ትዕግስት ወርቅነህ ፍፁም የተለያዩ አመለካከቶች እና የፓርቲ አቋም የያዙ ሰዎች በጋራ ሆነው ንግግር እንዲያደርጉ አካዳሚው እየሰራ ነው ሲሉ ለሸገር ነግረዋል፡፡
በተለያዩ ወቅቶች በዴሞክራሲ አካዳሚው ስልጠና መሰጠቱን የተናገሩት ወ/ት ትዕግስት ወጣት ሴቶች ለስልጠና የሚመጡት በአብዛኛው ከፖለቲካ ፓርቲ በመወከል ነው ይላሉ፡፡
አክቲቪስቶችም በስልጠናው ተሳትፈዋል ተብሏል፡፡
ፌዴራሊዝም ምንድነው ነው? ፖለቲካ ምንድነው? የሚሉ ሀሳቦችን ጨምሮ ሰልጣኞቹ አብረው በሚቆዩባቸው 21 ቀናት እና አንዱ የሌላውን ሀሳብ እንዲረዳና መግባባት እንዲፈጥሩ በጋራ የሚሰሯቸውን ስራዎች ይጭራልም ሲሉ ወ/ት ትዕግስት ነግረውናል፡፡
ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ….
የኔነህ ሲሳይ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
Website፡ https://www.shegerfm.com/
YouTube : https://shorturl.at/18TS1
Telegram : https://shorturl.at/68aeK
Facebook፡ https://shorturl.at/tm5Q4
WhatsApp : https://shorturl.at/8vwRx
X :- https://x.com/shegerfm?s=2
LinkedIn: https://shorturl.at/Vfe6i
Tiktok : https://shorturl.at/lhYiv
Instagram: https://shorturl.at/9X4S7





Comments