top of page

መጋቢት 13፣2016 - ''እንደ አክሱምና ላሊበላ ባሉ የቱሪዝም መዳረሻ ስፍራዎች የመግቢያ ዋጋ በእጥፍ ጨምሯል'' የኢትዮጵያ አስጎብኚ ማህበር

  • Mar 22, 2024
  • 1 min read

በተለያዩ የቱሪዝም መዳረሻ ስፍራዎች የሚታየዉ የዋጋ ጭማሪ ጊዜዉን ያገናዘበ አይደለም ተባለ፡፡


ይህንን ያለው የኢትዮጵያ አስጎብኚ ማህበር ነዉ፡፡


ማህበሩ እንደ አክሱምና ላሊበላ ባሉ የቱሪዝም መዳረሻ ስፍራዎች ጎብኚዎች የሚከፍሉትን የመግቢያ ዋጋ በእጥፍ ጨምሯል ብሏል፡፡


ይህ ደግሞ ጊዜውን የጠበቀ ጭማሪ አይደለም ሲል እየተቃወመዉ ነዉ፡፡


የኢትዮጵያ አስጎብኚ ማህበር የቦርድ አባል እና የሞንፔይ አስጎብኚ ድርጅት ባለቤት የሆኑቱን አቶ ያሬድ ሙሉጌታ ለሸገር እንደተናገሩት በዚህ ሰዓት ትኩረት ተሰጥቶ መሰራት ያለበት የጎብኚን ቁጥር ማሳደግ ላይ ነው ይላሉ፡፡


ኢትዮጵያ ውስጥ እየተሰራ ያለው ከዚህ ተቃራኒ ነው ያሉ ሲሆን እንደ ላሊበላ ያሉ የቱሪዝም መዳረሻ ስፍራዎች ለመግቢያ ያስከፍሉት የነበረዉ 50 ዶላር፤ አሁን ላይ ይህ ዋጋ እጥፍ ሆኖ ወደ 100 ዶላር አድጓል በማለት ነግረውናል፡፡


ዋጋ ጭማሪዉ የቱሪዝም ዘርፉ ከተቀዛቀዘበት እንዳይወጣ ሊያደርግ ስለሚችል ከወዲሁ ሊታሰብበት ይገባልም ብለዋል፡፡


የአማራ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ የቱሪዝም ልማት ዳይሬክተር አቶ መልካሙ አዳም በክልሉ ውስጥ ባሉ አንዳንድ የቱሪዝም መዳረሻ ስፍራዎች የዋጋ ጭማሪዎች እየታየ መሆኑን ታዝበናል ይላሉ፡፡


በአማራ ክልል አብዛኛዉ የቱሪዝም መዳረሻ ስፍራዎች ባለቤትነት የሀይማኖት ተቋማት ነዉ ያሉ ሲሆን የዋጋ ጭማሪ የታየውም በነዚህ ስፍራዎች ብቻ ነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡


መንግስት የሚያስተዳድራቸዉ የቱሪዝም መዳረሻዎች ምንም አይነት የዋጋ ጭማሪ አልታየባቸዉም ብለዋል፡፡



የኢትዮጵያ አስጎብኚ ማህበራት፤ የቱሪዝም ዘርፉ እንዲነቃቃ በተለያዩ ሀገራት የሚዘጋጁ የቱሪዝም አዉደርዕዮች ላይ እየተሳተፍኩ ነው ያለ ሲሆን አላማውም ነገሮች ሲስተካከሉ ጎብኚዎች የሀገሪቱ ቱሪዝም መጥተዉ እንዲጎበኙ ለማስተዋወቅ ነው ብለዋል አቶ ያሬድ፡፡


በረከት አካሉ



የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…




Recent Posts

See All
ከአምስት አመት በኋላ በምግብ እጥረት ምክንያት የሚቀነጭሩ ህጻናት እንዳይኖሩ በሰቆጣ ቃል ኪዳን የገባችው ኢትዮጵያ እስካሁን በከወነችው ስራ ምን ውጤት አገኘች?

ሰኔ 15/2018 ከአምስት አመት በኋላ በምግብ እጥረት ምክንያት የሚቀነጭሩ ህጻናት እንዳይኖሩ በሰቆጣ ቃል ኪዳን የገባችው ኢትዮጵያ እስካሁን በከወነችው ስራ ምን ውጤት አገኘች? በ2025 ስራውን በ700 ወረዳዎች ላይ ተግባራዊ አደርጋለሁ ብትልም እዛ ማድረስ ግን አልቻለችም ታዲያ ከ አምስት አመት በኋላ እንደቃሏ

 
 
 
የአሜሪካው የተራድኦ ድርጅት (USAID)ን ጨምሮ የተለያዩ አለማቀፍ የእርዳታ ድርጅቶች ስራቸውን ማቋረጣቸው እና እርዳታ መቀነሳቸው እያሳደረ ያለው ጫና ከፍ ያለ መሆኑ ይነገራል፡፡

ሰኔ 15/2018 የአሜሪካው የተራድኦ ድርጅት (USAID)ን ጨምሮ የተለያዩ አለማቀፍ የእርዳታ ድርጅቶች ስራቸውን ማቋረጣቸው እና እርዳታ መቀነሳቸው እያሳደረ ያለው ጫና ከፍ ያለ መሆኑ ይነገራል፡፡ በእዚሁ ምክንያት የኢትዮጵያ ቤተሰብ መምሪያ ግማሽ ያህል ሰራተኞቹን መቀነሱን እና የሰረዘው ፕሮጅክትም መኖሩን መናገ

 
 
 

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page