መድኃኒቶችን በአግባቡ አለመጠቀም፤ ዜጎች ወጪ አውጥተው ታክመውም እንዳይድኑ አንዱ ምክንያት እየሆነ ነው ተባለ፡፡
- 2 hours ago
- 1 min read
ሰኔ 8/2018
መድኃኒቶችን በአግባቡ አለመጠቀም፤ ዜጎች ወጪ አውጥተው ታክመውም እንዳይድኑ አንዱ ምክንያት እየሆነ ነው ተባለ፡፡
የሚታዘዙ መድኃኒቶችን በተገቢው እና በሀኪም ትዕዛዝ አለመወሰድ በሀገር ኢኮኖሚ ጉዳት እየደረሰ እና ዜጎችም ህይወታቸው እያጡ እንደሆነ ተነግሯል፡፡
ይህ ልማድ በተለይም የፀረ-ተህዋሲያን መድሃኒቶች ጀርሞች እንዲላመዷቸው ስለሚያደርግ፤ እያደረሰ ያለው ጉዳት ከፍተኛ እንደሆነ ተነግሯል፡፡

ይህንን ችግር ለመቀነስ ሰዎች የመድኃኒት አጠቃቀማቸው ላይ ከፍተኛ ጥንቃቄ ሊያደርጉ ይገባል ሲል የተናገረው የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለሥልጣን ነው።
ይህ ችግር ከኢትዮጵያም በተጨማሪ በአለም ደረጃ ስጋት እየሆነ ነው ተብሏል፡፡
የፀረ-ተህዋሲያን መድኃኒቶች በጀርሞች መለመድ (Antimicrobial Resistance / #AMR Day) የግንዛቤ ማስጨበጫ ቀን በኢትዮጵያ ለ14ኛ ጊዜ ዛሬ ተከብሯል።
የኢትዮጵያ የምግብና መድኃኒት ባለሥልጣን፣ የኢትዮጵያ ፋርማሲ ማህበር ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር ባዘጋጁት መድረክ ላይ ቀንኑ ስለ ጉዳዩ በሰፊው ተነስቷል፡፡

በዚህ የውይይት መድረክ ላይ የተገኙት የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ሄራን ገርባ፤ የፀረ-ተህዋሲያን መድሃኒቶች በጀርሞች መለመድ ችግር ለሀገር ከፍተኛ ጉዳት እያደረሰ እንደሚገኝ አንስተዋል፡፡
በዓለም አቀፍ ደረጃ በየዓመቱ ለ750 ሺህ ሰዎች በዚሁ ችግር የተነሳ ለሞት እንደሚዳረጉም አንስተዋል።
ከኢኮኖሚ አንጻርም በተለይ በአዳጊ ሀገራት 5 በመቶ ገደማ የኢኮኖሚ ኪሳራ እንደሚያደርስ በጥናቶች መረጋገጡንም አስታውሰዋል፡፡
ችግሩ እያደረሰ ኪሳራ እየሰፋ በመምጣቱ ቀድሞ በዘር የነበረውን መመሪያ ዳግም እንዲከለስ ተደርጓል ብለዋል፡፡
ከሀኪም ትዕዛዝ ውጪ መድሃኒቶችን ጨምሮና ወይም ቀንሶ መውሰድ፣ የግልና የአከባቢ ንፅህናን አለመጠበቅ እና መሰል ጥንቃቄ የጎደላቸው ተግባራት ችግሩን እንዲከሰት መንስኤዎች ኪሚሆኑ ልማዶች መካከል እንደሚጠቀሱ አስረድተዋል።

የኢትዮጵያ ፋርማሲ ማህበር ፕሬዝዳንት ዶ/ር ዳንኤል ዋቅቶሌ በበኩላቸው ችግሩን ለመቅረፍ ከባለሞያው እስከ ተጠቃሚው የጋራ ትብብር እንደሚሻም ተናግረዋል።
በክልሎችም ደረጃቸውን የጠበቁ የማህበረሰብ ፋርማሲዎች እንዲቋቋሙ ለማድረግ እየተሰራ እንደሆነ በመድረኩ ተነስቷል።
በኢትዮጵ አግባብ ያልሆነ የፀረ-ተዋህሲያን መድኃኒቶችን ከመጠቀም ጋር በተያያዘ ከፍተኛ ችግር ከሚታይባቸው መካከል፣ የቲቢ፣ የኤችአይቪ እና የወባ መድኃኒቶች ተጠቅሰዋል፡፡
ማንያዘዋል ጌታሁን ያዘጋጀውን በፋሲካ ሙሉወርቅ





Comments