top of page

መስከረም 30 2018 - የኢትዮጵያ የተቀማጭ ገንዘብ መድን ፈንድ በበጀት ዓመቱ የመጀመሪያ ሶስት ወራት ከ2 ቢሊዮን ብር በላይ ገንዘብ መሰብሰቡን ተናገረ፡፡

  • sheger1021fm
  • Oct 10
  • 1 min read

ተቋሙ እስካሁን የሰበሰብኩት አጠቃላይ የአረቦን ገንዘብ 15.93 ቢሊዮን ብር ደርሷልም ብሏል፡፡


የኢትዮጵያ የተቀማጭ ገንዘብ መድን ፈንድ በባንክና ማይክሮፋይናንስ ተቋማት ገንዘብ ያስቀመጡ ግለሰቦች ለሚገጥማቸው ችግር የኢንሹራንስ ሽፋን ለመስጠት የተቋቋመ ነው፡፡


አንድ የፋይናንስ ተቋም በኪሳራ ምክንያት ቢወድቅ፣ ፈንዱ ለእያንዳንዱ ገንዘብ አስቀማጭ እስከ 100,000 ብር ድረስ ተመላሽ ያደርጋል ተብሏል፡፡


የአረቦን ገንዘቡንም ከአባል ፋይናንስ ተቋማት እንደሚያሰባስብ ተነግሯል፡፡


የኢትዮጵያ የተቀማጭ ገንዘብ መድን ፈንድ በ2018 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት ከፋይናንስ ተቋማት 2.08 ቢሊየን ብር አረቦን ሰብስቤያለሁ ብሏል፡፡

ree

የአባል ፋይናንስ ተቋማት ተቀማጭ ገንዘብ በማደጉ የሰበሰብኩት ገንዘብ ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ጊዜ በ26.8 በመቶ ጨምሯል ሲል ተናግሯል።


ፈንዱ እስከዛሬ የሰበሰበው የአረቦን ገንዘብ 15.93 ቢሊየን ብር መድረሱንም ከላከልን መግለጫ ተመልክተናል፡፡


የተቀማጭ ገንዘብ መድን ፈንዱ እስካሁን ከሰበሰበው ገንዘብ ውስጥ 14.51 ቢሊየን ብሩ ከመደበኛ ተቀማጭ፣ 1.42 ቢሊየን ብሩ ደግሞ ከወለድ ነፃ ተቀማጭ ገንዘብ የተሰበሰበ ነው ብሏል፡፡


የሚሰበስበውን ገንዘብ በመንግስት ግምጃ ቤት ሰነድ ላይ ኢንቨስት እንደሚያደርግና በሙዳራባህ የቁጠባ ሂሳብ እንደሚያስቀምጥም ተነግሯል፡፡


አጠቃላይ የፈንዱ ኢንቨስትመንት 16.49 ቢሊየን ብር ደርሷል ተብሏል።


15.05 ቢሊየን ብሩ በመንግስት ግምጃ ቤት ሰነድ ኢንቨስት የተደረገ፣ ቀሪው 1.44 ቢሊየን ብር በሙዳራባህ የቁጠባ ኢንቨስትመንት ሂሳብ የተቀመጠ ነው ተብሏል፡፡


የኢትዮጵያ የተቀማጭ ገንዘብ መድን ፈንድ በ2018 በጀት ዓመት በአጠቃላይ 3.02 ቢሊየን ብር በአረቦን ለመሰብሰብ አስቤያለሁ ብሎ ተናግሯል፡፡


ቴዎድሮስ ወርቁ


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…


Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page