top of page

መስከረም 29 2018 - እንደ ኢትዮጵያ ባሉ የአፍሪካ ሀገራት በካንሰር የተያዙ ሰዎች በህይወት የመቆየት እድል 50 ከመቶ በታች እንደሆነ ተነግሯል።

  • sheger1021fm
  • Oct 9
  • 1 min read

ለዚህም ምክንያቱ ሰዎች በካንሰር ተይዘው ህመሙ ተባብሶ 3ኛ እና 4ኛ ደረጃ ላይ ከደረሰ በኋላ ሃኪም ቤት ስለሚመጡ ነው ተብሏል።


ይህ የተባለው ረዳት ሜዲካል ፕላዛ ከንጋት የጡት ካንሰር ታማሚዎች በጎ አድራጎት ቡድን ጋር በመተባበር በተካሄደ የጡት ካንሰር የግንዛቤ መስጫና ልምድ ማካፈል መድረክ ላይ ነው።


በመድረኩ የውይይት ተሳታፊ የነበሩት በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል የካንሰር ስፔሻሊስት ዶ/ር ወንጌል ፀጋ የጡት ካንሰር በ1ኛ እና 2ኛ ደረጃ በጊዜ ከታከመ 90 በመቶ የመዳን ዕድል አለው ብለዋል።


ባለሞያዋ ሰዎች ስለ ካንሰር ህመም ያላቸው ግንዛቤ አነስተኛ በመሆኑ መታከም ባለባቸው ሰዓት ህክምና ባለመውሰዳቸው ብቻ ህይወታቸውን እያጡ ነው ብለዋል።


ካንሰር 90 በመቶ በአኗኗር ዘይቤ የሚመጣ ህመም በመሆኑ የአመጋገብ ስርዓትን ማስተካከል እንደሚገባ ተነግሯል።


ከዚህም በተጨማሪ በየጊዜው የጡት ካንሰር ቅድመ ምርመራን በማድረግ ህመሙ ተባብሶ ወደ ከፋ ደረጃ ከመሻገሩ በፊት መቆጣጠርን ልምድ ማድረግ ያስፈልጋል ተብሏል።


ይህንንም ለማበረታታት ረዳት ሜዲካል ፕላዛ ለአንድ ወር ያህል የ20 በመቶ ቅናሽ የጡት ካንሰር የማሞግራፊ ምርመራ እንደሚያደርግ ተናግሯል።


ንጋት መኮንን


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…


Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page