መስከረም 29 2018 - በአፍሪካ የንግድ ቀጠና ስምምነት መግባት ለሀገር ውስጥ ነጋዴ፣ ለሸማቹ እና በአጠቃላይ በንግድ ስርዓቱ ውስጥ ይዞ የሚመጣው እድልና ተፅእኖ ምንድን ነው?
- sheger1021fm
- Oct 9
- 1 min read
የስጋ፣ አትክልትና ፍራፍሬ ምርቶችን በመላክ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጠናውን እንደምትቀላቀል ተነግሯል።
ለመሆኑ ወደዚህ ንግድ መግባቱ ለሀገር ውስጥ ነጋዴ፣ ለሸማቹ እና በአጠቃላይ በንግድ ስርዓቱ ውስጥ ይዞ የሚመጣው እድልና ተፅእኖ ምንድን ነው?
በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የምግብና ሥነ-ምግብ ትምህርት ክፍል ተባባሪ ፕሮፌሰር እና የኢትዮጵያ የሸማቾች ጥበቃ ድርጅት የቦርድ አባል የሆኑት አሻግሬ ዘውዱ(ዶ/ር)፤ ይህ ሂደት ለሀገር ውስጥ ሸማች ምርትን በአማራጭ፣ በጥራትና በተሻለ ዋጋ እንዲያገኝ የሚያደርገው ነው ብለዋል።
የተለያዩ ሀገሮች ምርታቸውን ከቀረጥ ነፃ ስለሚያስገቡ ሸማቹ ተጠቃሚ መሆኑ ጥርጥር የለውም ብለዋል።
ወደ ሌሎቹ ሀገሮች ኢትዮጵያ ምርቷን በብዛት ለመላክና ለመወዳደር ግን በጥራት እና በሌላውም መመዘኛ በደንብ መስራትን የሚጠይቅ እንደሚሆን አንስተዋል።
የሀገር ውስጥ ነጋዴውም ለተወሰነ ጊዜ በዚህ ውስጥ የመዝለቅ ፈተና ሊገጥመው ይችላል ብለዋል።
በየጊዜው ውጤትና ችግሩን እየፈተሹ እያረሙ መሄድም እንደ ሀገር የሚጠበቅ ስራ መሆኑን አብራርተዋል።
ቴዎድሮስ ወርቁ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
🌐Website፡ https://www.shegerfm.com/
🎥YouTube https://tinyurl.com/37tux478
🟦Telegram https://t.me/ShegerFMRadio102_1
📘Facebook፡ https://tinyurl.com/4tx8t8wm
💬WhatsApp ፡ https://tinyurl.com/ycxjmm3s












Comments