top of page

መስከረም 29 2018 - ‘’በአማራ ክልል ትምህርት በተጀመረባቸው አካባቢዎች የሰላም ዋስትና ሊሰጥ የሚችለው ህብረተሰቡ ነው’’ ሲል ክልሉ ተናገረ፡፡

  • sheger1021fm
  • Oct 9
  • 1 min read

‘’በአማራ ክልል ትምህርት በተጀመረባቸው አካባቢዎች የሰላም ዋስትና ሊሰጥ የሚችለው ህብረተሰቡ ነው’’ ሲል ክልሉ ተናገረ፡፡


የአማራ ክልል የመንግስት ኮሚኒኬሽን በቅርቡ በክልሉ ስላለው የትምህርት ሁኔታ ከጋዜጠኞች ጋር በነበረው ውይይት ‘’መንግስት የክልሉን ፀጥታ ለማስጠበቅ እየሰራ ነው’’ ብሏል፡፡


የአማራ ክልል የመንግስት ኮሚኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ መንገሻ ፋንታው(ዶ/ር) ‘’ችግር ባለባቸው አካባቢዎች በሙሉ መንግስት ወታደር ማቆም አይችልም ይሄ ትክክል አይደለም’’ ሲሉ ተናግረዋል፡፡


ትምህርት ከዚህ እሳቤ መውጣት አለበት የሚሉት ዶክተር መንገሻ ‘’የሰላም ዋስትና መስጠት የሚችለው ከመንግስት ይልቅ እራሱ ህብረተሰቡ ነው’’ ሲሉም ጠቅሰዋል፡፡


#አማራ_ክልል የመንግስት ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎችም በክልሉ እየተዋጉ ያሉ ቡድኖች ለድርድር ዝግጁ ከሆኑ ክልሉ ለዚህ መዘጋጀቱን ብዙ ጊዜ ተናግረዋል ግን ከዚያ ወገን ምንም መልስ እየመጣ አይደለም ብለዋል፡፡


በአማራ ክልል የተቋቋመው የሰላም ካውንስል የፀጥታ ችግሩን ለመፍታት ተደጋጋሚ ሙከራዎችን አድርጎ አልተሳካለትም መባሉንም ሰምተናል።


ከዛም ባለፈ እገታ ተፈፅሞባቸው የተለቀቁ የሰላም ካውንስል አባላት እንዳሉም የአማራ ክልል የመንግስት ኮሚኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ መንገሻ ፋንታው(ዶ/ር) አስረድተዋል፡፡


ሰሞኑን በአማራ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች ግጭት እየተደረገ መሆኑን የጠቀሱት ዶክተር መንገሻ ፋንታው፣ መንግስት እያደረገ ያለውን የሰላም ጥሪ ተቀብለው ወደ ህብረተሰቡ የሚቀላቀሉ ታጣቂዎች እንዳሉም አንስተዋል፡፡


‘’በአማራ ክልል ያለውን የፀጥታ ችግር ለመፍታት የክልሉ መንግስት ዝግጁ ነው’’ ያሉት የክልሉ የመንግስት ኮሚኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ ድርድር ለማድረግ ፍቃደኛ መሆኑንም አንስተዋል፡፡


በዚህ ጉዳይ ከክልሉ የኃይማኖት አባቶችና ከሀገር ሽማግሌዎች ጋር ተደጋጋሚ ምክክር ማድረጋቸውንም ጠቅሰዋል፡፡


በረከት አካሉ


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…


Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page