መስከረም 29 2018 - ስነ ተዋልዶን በተመለከተ ፖሊሲዎች ቢኖሩም ተግባራዊነታቸው ዝቅተኛ መሆኑን በዘርፉ የሚሰሩ ድርጅቶች ተናገሩ
- sheger1021fm
- 2 days ago
- 1 min read
Updated: 1 day ago
ስነ ተዋልዶን በተመለከተ ፖሊሲዎች ቢኖሩም ተግባራዊነታቸው ዝቅተኛ መሆኑን በዘርፉ የሚሰሩ ድርጅቶች ተናገሩ።
በተለይም አካል ጉዳተኞች እና የተገለሉ የሚባሉ የህብረተሰብ ክፍሎች የስነ ተዋልዶ አገልግሎት በማግኘቱ እየተቸገሩ እንደሆነ ድርጅቶቹ አስረድተዋል።
እኛ ይህንን የሰማነው በሜክ ዌይ(Make Way) የ5 ዓመት ፕሮጀክት፤ ከአጋር አካላት ጋር በስነ ተዋልዶ ጤና አገልግሎት ዙሪያ ተሰርተዋል የተባሉ ስራዎች በተመለከተ ማብራሪያ በሰተጠበት መድረክ ላይ ነው።

በተለያዩ አካባቢዎች የተፈጠሩ የፀጥታ ችግሮችም የስነ ተዋልዶ አገልግሎት መሰጠት አለባቸው ባልናቸው ቦታዎች ገብተን እንዳንሰራም እንቅፋት ሆነውብናል ብለዋል ድርጅቶቹ።
ተመስገን ጥላሁን(ዶ/ር) ቪኤስኦ(VSO) የተሰኘ ድርጅት የኢትዮጵያ ተወካይ ሲሆኑ በኢትዮጵያ በርካታ ወጣቶች በስነ ተዋልዶ ዙሪያ ያላቸው ግንዛቤ አናሳ እንደሆነ አንስተው ይህንን ክፍተት ለማስተካከል በፖሊሲ ተፈፃሚነት ላይ መንግስትና የሚመለከታቸው በብርቱ ሊሰሩበት ይገባል ሲሉ ነግረውናል።
ይህ ችግር ለመቀነስም ድርጅታቸው ከ40 የጤና ተቋማት ጋር በጋራ እየሰራ እንደሆነም አንስተዋል።
ፖሊሲዎች ወጥተዋል ሲባል ይሰማል ነገር ግን ትግበራው ላይ ችግር አለ ሲሉ የነገሩን ደግሞ የ'ሜክ ዌይ' የኢትዮጵያ ዳይሬክተር ነጋሽ ኡስማን ናቸው።
በዘርፉ ያለውን የግንዛቤ ክፍተት እና ተያያዥ ችግሮችን ለመቀነስም ከሚመለከታቸው እና ከመንግስት አካላት ጋር እየተነጋገርን ነው ብለዋል፡፡
በ5 ዓመቱ ኘሮጀክት በቀጥታ በስነ ተዋልዶ ጤና ዙሪያ ስልጠና እና የግንዛቤ ስራን ጨምሮ በተለያየ መንገድ 50,000 ሰዎች በቀጥታ ተጠቃሚ ሆነዋል ብለውናል፡፡ ለዚህም 70 ሚሊየን ብር ወጪ ተደርጓል መባሉንም ሰምተናል።
ማንያዘዋል ጌታሁን
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
🌐Website፡ https://www.shegerfm.com/
🎥YouTube https://tinyurl.com/37tux478
🟦Telegram https://t.me/ShegerFMRadio102_1
📘Facebook፡ https://tinyurl.com/4tx8t8wm
💬WhatsApp ፡ https://tinyurl.com/ycxjmm3s
👔LinkedIn ፡ https://tinyurl.com/tyfaekvx