top of page

መስከረም 28 2018 - ኢትዮጵያ የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ ያሉኝ ሀብቶች ምን ምን ናቸው? ብላ እያስጠናች ነው ተባለ

  • sheger1021fm
  • Oct 8
  • 1 min read

ኢትዮጵያ የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ ያሉኝ ሀብቶች ምን ምን ናቸው? በየትኞቹስ አካባቢዎች ይገኛሉ ብላ እያስጠናች ነው ተባለ፡፡


ከዚህ አስቀድሞ 16 ዓመት የቆየውን #የቱሪዝም_ፖሊሲ ተሻሽሎ እስከሚጸድቅ እየተጠበቀ እንደሆነም የቱሪዝም ሚኒስትሯ ተናግረዋል፡፡


ዘርፉን ለማሳደግ የተሻለ ገቢ ለማግኘት የቱሪዝም መዳረሻ የሚባሉ የመስህብ ቦታዎችን መለየትና በማደስ፣ በመጠበቅ ለሀገር ውስጥም ይሁን ለውጪ ጎብኚዎች ክፍት ማድረግና መሰረተ ልማቶችን ማሟላት እንደሚያስፈልግም ተነግሯል፡፡


በዚህም ኢትዮጵያ ያላትን ሀብት መለየትና የት ቦታ ምን አለ? የሚለውን ማወቅ አለባትም ተብሏል፡፡


አሁን ላይ በሲዳማ ክልል የቱሪዝም መስህብ መሆን የሚችል ምን አለ? ተብሎ ጥናት ተደርጎ እንደተጠናቀቀ እና ይህንን ጥናት በሁሉም የኢትዮጵያ ክልሎች ለማድረግ አቅደናል ሲሉ የቱሪዝም ሚኒስትሯ ሰላማዊት ካሣ ተናግረዋል፡፡


የቱሪዝም ሚኒስቴር በዚህ ዓመት ከሚሰራቸው ስራዎች መካከል አንዱ አገልግሎቱን ማሳደግ እንደሆነና ብቻውን ሳይሆን የሚመለከታቸውን በማሳተፍ እንደሚሰራው አስረድተዋል፡፡


በተለይ የዘርፉ ትልቅ ችግር በዘርፉ የሰለጠኑ የሰው ኃይል አለመኖሩ ነው ያሉት ሚኒስትሯ ከቱሪዝም የሞያ ማሰልጠኛዎች ጋር በመስራት ችግሩ ለማቃለል እንሞክራለን ብለዋል፡፡


ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ….


ማርታ በቀለ


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…


Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page