top of page

መስከረም 28 2018 - ኢትዮጵያ ወረርሽኞችን የሚያስከትሉትን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጽእኖ ለመቀነስ ተሰናድታ መጠበቅ አለባት ተብሏል

  • sheger1021fm
  • Oct 8
  • 1 min read

ዓለም በየጊዜው አዳዲስ እንዲሁም ዓይነታቸው የሚለዋወጥ ወረርሽኞች እያስተናገደች ነው፤ እንደ ኮቪድ 19 ያሉት ደግሞ ከፍተኛ ተጽዕኖ በሁሉም መስክ አሳድረዋል፡፡


ኢትዮጵያ ወቅታዊ ወረርሽኞችን በተመለከተ የሚያስከትሉትን የጤና ጉዳት በተጨማሪም በማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ መስኮች የሚደርሰውን ተጽእኖ ለመቀነስ ተሰናድታ መጠበቅ አለባት ተብሏል።


ለዚህም ለመጪዎቹ አምስት ዓመታት ያህል የሚሰራበትን ስትራቴጂ በቅርቡ ይፋ አድርጋለች፡፡


በአለም አቀፍ ደረጃ የወረርሽኞች ስፋት እንዲሁም የመከሰት መጠን እየጨመረ መምጣቱን የሚናገሩት በኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የአለም አቀፍ የጤና ደንብ እና የአንድ ጤና ጽህፈት ቤት ሀላፊ የሆኑት ዶክተር ፈይሳ ረጋሣ ይህንንም ለመቋቋም ሀገራት ራሳቸውን ማዘጋጀት እንዳለባቸው እና ኢትዮጵያም በዚህ ላይ እየሰራች መሆኑን ይጠቅሳሉ፡፡

ree

የበሽታዎች ክስተት እና ስርጭት እየበዛ በመምጣቱ ሀገራት እነዚህ በሽታዎች የመከላከልና የመቆጣጠር አቅም መገንባት አለባቸው፤ ለመገንባት ደግሞ ብሔራዊ የጤና ደህንነት መርሀ ግብር አቅደው ወደ ትግበራ መግባት አለባቸው ብለዋል፡፡


ኢትዮጵያ ላይ ጨምሮ የወረርሽኞች ስፋት እየጨመረ ስለመጣ ሀገራት የመከላከል የመቆጣጠር እና የምላሽ አቅም መገንባት አለባቸው ለዚህም በሽታዎችን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የዝግጅት አቅም የሚገነባ ስትራቴጂ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡


ኢትዮጵያ ከዚህ ቀደም ወቅታዊ ወረርሽኞችን የምትከላከልበት እና የምትቋቋምበት ዕቅድ አዘጋጅታ ነበር የሚሉት ዶክተር ፈይሳ ሁለተኛው ዕቅድ ሲሰናዳ ከዚህ ልምድ ተወስዶ ነው ይላሉ፡፡


ከጤና ደህንነት ጋር በተያያዘ የሚሰራባቸው የተመረጡ ጉዳዮች አሉ ያሉት ዶክተር ፈይሳ በሰዎች ጤና ላይ አዳዲስ የሚከሰቱ ወረርሽኞች፣ መድሀኒት የተላመዱ ህመሞች እንዲሁም ከእንስሳት ወደ ሰዎች የሚተላለፉ ህመሞች ዋና ዋናዎቹ ናቸው ማቀዱ ላይ ብቻ ሳይሆን ግን የመከላከል እንዲሁም የህክምና ስራዎችም ግን ትኩረት ይፈልጋሉ ተብሏል፡፡


የአንድ ጤና እንዲሁም ሀገራዊ የጤና ደህንነትን ለመተግበር በአጠቃላይ 20 የሚሆኑ የሀገር ቤት እንዲሁም የአለም አቀፍ ተቋማት የሚሳተፉበት ሲሆን ለስራውም የሚወጣው ወጪ በመንግስት እንዲሁም በአለም አቀፍ ለጋሽዎች የሚሸፈን መሆኑ ተነግሯል፡፡


ምህረት ስዩም


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…


Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page