መስከረም 28 2018 - ''ኢትዮጵያ ከውጪ የምታገኘው እርዳታ ማሽቆልቆሉን በጥናት አረጋግጫለው'' የኢትዮጵያ ኢኮኖሚክስ አሶሴሼን
- sheger1021fm
- Oct 8
- 1 min read
መስከረም 28 2018
የኢትዮጵያ ኢኮኖሚክስ አሶሴሼን ባለፉት 2 ዓመታት ኢትዮጵያ ከውጪ የምታገኘው እርዳታ ማሽቆልቆሉን ባደረግሁት ጥናት አረጋግጫለው አለ።
በተለይ ከ4 ዋና ዋና አበዳሪዎች ማለትም ፈረንሳይ፣ ጀርመን፣ እንግሊዝ እና አሜሪካ ለተከታታይ 3 ዓመታት የተገኘው እርዳታ እንደቀነሰ በጥናቴ አረጋግጫለሁ ብሏል።
በየጊዜው ለኢትዮዽያ ኢኮኖሚ የሚበጀውን ሀሳብ የሚያዋጣውና የሚመክረው የኢትዮዽያ የኢኮኖሚክስ አሶሴሽን ተመራማሪዎች እና አጥኝዎች ሰሞኑን በኢትዮዽያ የውጪ እዳ ጫና እና እርዳታ መዳከም ዙሪያ መምከራቸውን ሰምተናል።
በተለይ ለኢትዮዽያ ይደረግ የነበረው #የውጪ_እርዳታ መቀነሱ የሚያመጣው ጫና እንዳለ በጥናቱ መብራራቱ ታውቋል።
በህፃናት፣ በፋይናንስ አካታችነት፣ በወጣቶች ስራ ፈጠራ፣ በሴቶች እና ተያያዥ ጉዳዮች የተቋረጠው እርዳታ ምን ጫና አመጣ ኢትዮዽያስ ምን ማድረግ ይኖርባታል በሚለው ጉዳይ ምሁራኑ መምከራቸውን ሰምተናል።
አዲስ ካሳሁን(ዶ/ር) በኢትዮዽያ ኢኮኖሚክስ አሶሴሽን ምክትል ፕሬዝዳንት ናቸው።
የአለም አቀፍ እርዳታ በዚህ ሁለት ዓመት በጣም እየወረደ መሆኑን ጠቅሰው በሁለት ዓመት ውስጥ ከ 9 እስከ 17 በመቶ ማሽቆልቆሉን ነግረውናል።
ይህም በኢኮኖሚው ላይ ተፅዕኖን እነደሚያሳድር ጥናቱ አሳይቷል ተብሏል።
በኢትዮዽያ ጥብቅ የገንዘብ ስርዓት ፖሊሲ በመተግበሩ የዋጋ ግሽበቱ እንደቀነሰ፣ ተጠባባቂ የውጪ ምንዛሪ ክምችት መጨመሩ እና አጠቃላይ የማክሮ ኢኮኖሚው ለውጥ እንደመጣበት በመንግስት በኩል ተደጋግሞ መነገሩ ይታወቃል።
ተህቦ ንጉሴ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
🌐Website፡ https://www.shegerfm.com/
🎥YouTube https://tinyurl.com/37tux478
🟦Telegram https://t.me/ShegerFMRadio102_1
📘Facebook፡ https://tinyurl.com/4tx8t8wm
💬WhatsApp ፡ https://tinyurl.com/ycxjmm3s
👔LinkedIn ፡ https://tinyurl.com/tyfaekvx












Comments