top of page

መስከረም 27 2018 ወጋገን ባንክ ባለፈው በጀት ዓመት በታሪኬ ከፍተኛውን ገቢና ትርፍ ያገኘሁበት ነበር አለ።

  • sheger1021fm
  • Oct 7
  • 1 min read

ባንኩ 13.5 ቢሊዮን ብር ገቢ ማግኘቱን የአንድ አክሲዮን ትርፍ  46.10 በመቶ መሆኑን አስረድቷል።

 

ባንኩ ዛሬ ባካሄደው 32 መደበኛ የባለአክሲዮኖች ጠቅላላ ጉባኤ የባንኩ የቦርድ ሰብሳቢ አቶ አብዲሹ ሁሴን ባንኩ እ.ኤ.አ በ2024/25 በጀት ዓመት ሪፖርት አቅርበዋል።

 

በዚህም ወጋገን ባንክ በታሪኩ ከፍተኛ የሆነውን  13.5 ቢሊዮን ብር ገቢ ማግኘቱን ፣ ይህም ካለፈው በጀት ዓመት ጋር ሲነፃፀር የ38 በመቶ እድገት እንደሚያሳይ ጠቁመዋል፡፡

 

ባንኩ ከታክስ በፊት  3.85 ቢሊዮን  ብር ትርፍ አግኝቷል ይህም ለመጀመሪያ ጊዜ የተመዘገበ ከፍተኛው ትርፍ መሆኑን የቦርድ ተሰብሳቢው ጠቅሰዋል።

 

ree

ትርፉ  ከባለፈው በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር የ73 በመቶ ብልጫ እንዳለው በሪፖርቱ ተጠቅሷል፡፡

 

የወጋገን ባንክ የተከፈለ ካፒታል በበጀት ዓመቱ መጨረሻ  7 ቢሊዮን ብር መድረሱን፣ናይህም ብሔራዊ ባንክ ካስቀመጠው የባንኮች ዝቅተኛ የተከፈለ ካፒታል መስፈርት በላይ መሆኑ ተነግሯል፡፡

 

የባንኩ ጠቅላላ ካፒታል 12.8 ቢሊዮን ብር ፣ጠቅላላ ሀብቱ ደግሞ  84.7 ቢሊዮን ብር  መድረሱን  የቦርድ ሰብሳቢው በሪፖርታቸው አስረድተዋል፡፡

 

በበጀት ዓመቱ የባንኩ ተቀማጭ ገንዘብ የ28 በመቶ እድገት በማስመዝገብ  66.5 ቢሊዮን ብር  መድረሱ ተጠቅሷል፡፡

 

ባንኩ ለተለያዩ የኢኮኖሚ ዘርፎች የሰጠው ብድርብር 53.5 ቢሊዮን መድረሱ የተነገረ ሲሆን ይህም ከባለፈው በጀት ዓመት አንፃር የ18 በመቶ እድገት እንደሚያሳይ ተጠቅሷል፡፡

 

የወጋገን ባንክ ዋና ስራ አስፈፃሚ አክሊሉ ውበት (ዶ/ር) በበኩላቸው ባንኩ በዘርፉ የሚስተዋሉ ተለዋዋጭ እና ፈታኝ ሁኔታዎችን ተቋቁሞ የላቀ ውጤት እያስመዘገበ መቀጠሉን ጠቅሰዋል፡፡

 

ያለፈው በጀት ዓመት ወጋገን ባንክ በኢትዮጵያ የሰነደ መዓለ ንዋዮች ገበያ ላይ ቀዳሚ ሆኖ ከመመዝገቡም በላይ ወጋገን ካፒታል የተሰኘ በሃገሪቱ የመጀመሪያ የግል ኢንቨስትመንት ባንክ አቋቁሞ ወደ ስራ አስገብቷል  ሲሉ ስራ አስፈፃሚው  አስታውሰዋል፡፡

 

ወጋገን ባንክ ቅርንጫፎቹ  455፣ የባለአክሲዮኖች ብዛት ደግሞ 14,871 መድረሱ ተነግሯል፡፡

 

ንጋቱ ሙሉ

 

የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

 

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page