መስከረም 27 2018 - ኮምፓስ ፕሮፐርቲስ እና ጎህ ቤቶች ባንክ በጋራ ሆነው በአይነቱ አዲስ ነው ያሉትን የቤት ግንባታ ፕሮጀክት ዛሬ ይፋ አድርገዋል።
- sheger1021fm
- Oct 7
- 1 min read
ኮምፓስ ፕሮፐርቲስ እና ጎህ ቤቶች ባንክ በጋራ ሆነው በአይነቱ አዲስ ነው ያሉትን የቤት ግንባታ ፕሮጀክት ዛሬ ይፋ አድርገዋል።
አሰራሩም በቅድሚያ አንድ ቤት ፈላጊ ወደ ኮምፓስ ፕሮፐርቲስ በመሄድ የሚፈልውን አይነት ቤት መርጦ ፎርም ይሞላል፡፡
ቀጥሎም ወደ በጎህ ቤቶች ባንክ በመሄድ በግሉ አካውንት ከፍቶ ተቀማጭ 500,000 ብር መክፈልና በየወሩ መቆጠብ አለበት ተብሏል፡፡
በዚህ ሂደት ውስጥ ገንዘቡ በራሱ በግለሰቡ አካውንት የሚቀመጥ እንጂ ወደ ኮምፓስም ሆነ ወደ ጎህ አካውንት የሚገባ ምንም አይነት ገንዘብ አይኖርም ብለዋል።
ቤት ፈላጊው የቆጠበው ገንዘብ ከግል አካውንቱ ወጥቶ ወደ ቤት ገንቢው ኮምፓስ ፕሮፐርቲስ የሚተላለፈው ቤቱ ተጠናቅቆለት ካርታ ሲረከብ ብቻ መሆኑን ሰምተናል፡
ቆጣቢው 15 በመቶ ወለድ ይታሰብለታል፣ በሂደት ይቅርብኝ ብሎ የቆጠበውን ገንዘብ ማውጣት ከፈለገም ለባንኩ ቀድሞ በማሳወቅ ማዉጣት ይችላል ተብሏል፡፡
ደንበኛው ገንዘቤን ላውጣ በማለቱ ምንም አይነት የአገልግሎት ክፍያም ሆነ ቅጣት ክፍያ የለውም ሲሉ የኮምፓስ ፕሮፐርቲስ እና ጎህ ቤቶች ባንክ ሀላፊዎች አስረድተዋል፡፡
የባንክ እገዛ የሚፈልግ ደንበኛም ቀሪ ክፍያውን ከባንክ ጋር በማያያዝ ቤቱን መረከብ እንደሚችል ተጠቅሷል፡፡
አሰራሩ ከተማው ላይ ከሪል ስቴት ጋር ተያይዞ በተደጋጋሚ የሚሰማውን ቅሬታ እና ችግር በእጅጉ ይቀርፈዋል የሚል እምነት እንዳላቸውም ኮምፓስ ፕሮፐርቲስ እና ጎህ ቤቶች ባንክ ጠቁመዋል።
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
🌐Website፡ https://www.shegerfm.com/
🎥YouTube https://tinyurl.com/37tux478
🟦Telegram https://t.me/ShegerFMRadio102_1
📘Facebook፡ https://tinyurl.com/4tx8t8wm
💬WhatsApp ፡ https://tinyurl.com/ycxjmm3s
👔LinkedIn ፡ https://tinyurl.com/tyfaekvx











Comments