መስከረም 27 2018 - ኢትዮጵያ የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ ንግድ ስምምነትን ማጠናቀቋን ተከትሎ በሸቀጦች ንግድ ዘርፍ መስከረም 29/2018 በይፋ ትጀምራለች ተባለ
- sheger1021fm
- Oct 7
- 1 min read
ኢትዮጵያ የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ ንግድ ስምምነትን ማጠናቀቋን ተከትሎ በሸቀጦች ንግድ ዘርፍ መስከረም 29/2018 በይፋ ትጀምራለች ተባለ፡፡
ይህንን ያሉት የንግድ ትስስርና ወጪ ንግድ ፕሮሞሽን ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታዋ ወ/ሮ ያስሚን ውሀብረቢ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ነው፡፡
በዚህም የመጀመሪያው የንግድ ልውውጥ በምስራቅና በደቡብ አፍሪካ ሀገራት ላይ እንደሚደረግ ተነግሯል፡፡

በማስጀመሪያ ንግዱ በኢትዮጵያ አየር መንገድ ካርጎ፤ ሥጋ፣ አትክልትና ፍራፍሬ እንዲሁም በየብስ ትራንፖርት ቡና፣ የጥራጥሬ ምርቶችና የቅባት እህሎች ወደ ኬንያ፣ ሶማሊያ እና ወደ ደቡብ አፍሪካ ይላካል ብለዋል፡፡
አህጉራዊ ነፃ ንግድ ስምምነቱ ትግበራው ለኢትዮጵያ ከፍተኛ ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታዎች ይኖሩታል ያሉት ሚኒስትር ዴኤታዋ ለኢትዮጵያ ንግድ ተወዳዳሪነትና ኢንቨስትመንትን ያነቃቃል፣ ሰፊ የሥራ ዕድል ይፈጥራል ሲሉ አስረድተዋል፡፡
ለሸማቹ ህብረተሰብ የተሻለ አማራጭ የምርት አቅርቦት ያስገኛል ብለዋል፡፡
የጉምሩክ ሂደቶችን ማዘመን እና የምርቶችን ጥራት መጠበቅ እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል፡፡
ማርታ በቀለ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
🌐Website፡ https://www.shegerfm.com/
🎥YouTube https://tinyurl.com/37tux478
🟦Telegram https://t.me/ShegerFMRadio102_1
📘Facebook፡ https://tinyurl.com/4tx8t8wm
💬WhatsApp ፡ https://tinyurl.com/ycxjmm3s
👔LinkedIn ፡ https://tinyurl.com/tyfaekvx











Comments