መስከረም 27 2018 - ት/ት ሚኒስቴር በ2018 የት/ት ዘመን በረመዲያል መርሀግብር ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚስገባውን ነጥብ ይፋ አድርጓል
- sheger1021fm
- Oct 7
- 1 min read
ትምህርት ሚኒስቴር በ2018 የትምህርት ዘመን በረመዲያል መርሀግብር ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚስገባውን ነጥብ ይፋ አድርጓል፡፡
ሚኒስቴሩ በግልም ሆነ በመንግስት ተቋማት #የረመዲያል_ፕሮግራም ለመከታተል የሚችሉት፤ እንደተፈተኑት የትምህርት አይነት ብዛት 33 ከመቶ እና ከዚያ በላይ ያስመዘገቡ ተማሪዎች መሆኑን ተናግሯል።
በዚህም የተፈጥሮ እና የማህበራዊ ሳይንስ ወንድ ተማሪዎች፤ 216 እና ከዚያ በላይ ያመጡ፣
የተፈጥሮ እና የማህበራዊ ሳይንስ ሴት ተማሪዎች 204 እና ከዚያ በላይ ያመጡ፣
የተፈጥሮ እና የማህበራዊ ሳይንስ መስማት የተሳናቸው ተማሪዎች በሁለቱም ፆታ 198 እና ከዚያ በላይ ያመጡ እንዲሁም
የተፈጥሮ እና የማህበራዊ ሳይንስ ዓይነ ስውራን ተማሪዎች በሁለቱም ፆታ 165 እና ከዚያ በላይ ያመጡ የሪሜዲያል ትምህርትን መከታተል እንደሚችሉ ትምህርት ሚኒስቴር በማህበራዊ የትስስር ገጹ አሳውቋል፡፡
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
🌐Website፡ https://www.shegerfm.com/
🎥YouTube https://tinyurl.com/37tux478
🟦Telegram https://t.me/ShegerFMRadio102_1
📘Facebook፡ https://tinyurl.com/4tx8t8wm
💬WhatsApp ፡ https://tinyurl.com/ycxjmm3s
👔LinkedIn ፡ https://tinyurl.com/tyfaekvx












Comments