top of page

መስከረም 26 2018 - በተያዘው የበጀት ዓመት 9 በመቶ ጠቅላላ የሀገር ውስጥ ምርት እድገትን የማሳካት ግብ መቀመጡ ተነገረ፡፡

  • sheger1021fm
  • Oct 6
  • 1 min read

በተያዘው የበጀት ዓመት 9 በመቶ ጠቅላላ የሀገር ውስጥ ምርት እድገትን የማሳካት ግብ መቀመጡ ተነገረ፡፡


በበጀት ዓመቱ #የዋጋ_ንረትን ወደ ነጠላ አሀዝ እንዲወርድ ይደረጋልም ተብሏል፡፡

ree

በህዝብ እንደራሴዎችና የፌዴሬሽን ምክር ቤት መክፈቻ ላይ ንግግር ያደረጉት ፕሬዘዳንት ታዬ አፅቀስላሴ የኢትዮጵያ ግብርና በተፈጥሮ ላይ መሰረት ያደረገ፤ ፍላጎቱ ደግሞ በውጪ ምርቶች ላይ ጥገኛ የሆነ ነው ብለዋል፡፡


ይህም ኢትዮጵያን ለአለም አቀፍ ተለዋዋጭ ሁኔታ ተጋላጭ አድርጓታል ብለዋል፡፡


እነዚህን ፈተናዎች መቋቋም የሚችል መንገድን መከተል የግድ እንደሚልም አንስተዋል፡፡


ምርት እና ምርታማነትን ፣ በዓይነትም በመጠንም የማሳደግ ስራ በተያዘው የበጀት አመት ይሰራል ያሉት ፕሬዘዳንት ታዬ ይህንኑ በማድረግ የሀገር ውስጥ ምርት እድገትን ዘጠኝ በመቶ ማድረግ የዋጋ ግሽበቱንም ወደ ነጠላ አሀዝ ማውረድ የመንግስት ግብ ይሆናል ብለዋል፡፡


ቴዎድሮስ ወርቁ


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…


Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page