top of page

መስከረም 23 2018 - ''በዚህ ዓመት ወደ ት/ት ገበታ ይመጣል ተብሎ ከታቀደው ተማሪ 26 ከመቶው ወደ ት/ቤት አልመጣም'' ትምህርት ሚኒስቴር

  • sheger1021fm
  • Oct 3
  • 1 min read

በአማራ ክልል በ2018 ዓ.ም ወደ ትምህርት ቤት ይመጣሉ ከተባሉ ተማሪዎች 53.7 ከመቶው እስካሁን አልተመዘገቡም ተባለ።


ይህ የተነሳው በትምህርት ችግር ዙሪያ ክልሉ ከመገናኛ ብዙሃን ጋር እያደረገ ባለው ውይይት ላይ ነው።


እንደ ሃገር በዚህ ዓመት ወደ ትምህርት ገበታ ይመጣል ተብሎ ከታቀደው ተማሪ አኳያ 26 ከመቶው ወደ ትምህርት ቤት አልመጣም ሲል ትምህርት ሚኒስቴር ተናግሯል።


የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ አየለች እሸቴ እንደ ሃገር በዚህ ዓመት ይመዘገባል ተብሎ ከታቀደው አኳያ 74 ከመቶ የሚሆነውን ማሳካት ተችሏል ብለዋል።


#አማራ_ክልል ለ2018 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ለመመዝገብ ከታቀደው 7.4 ሚሊዮን ተማሪዎች ውስጥ የተመዘገቡ ተማሪዎች 46.3 ከመቶ ወይም 3.4 ሚሊዮን ተማሪዎች ብቻ ናቸው ብለዋል።


3.9 ሚሊዮን የመሆነው ተማሪ አሁንም ድረስ እቤቱ መቀመጡን የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ጠቅሷል።


ክልሉ ውስጥ ካሉ 11,000 ትምህርት ቤቶች ውስጥ 8624 የሚሆኑት ብቻ ተማሪ ተቀብለው እያስተማሩ ነው ተብሏል።


ከሰሜኑ ጦርነት ጀምሮ እስካሁን በክልሉ ባለው ችግር ምክንያት 6154 የሚሆኑ ትምህርት ቤቶች ጉዳት ደርሶባቸዋል ተብሏል።


ከዚህ ውስጥ 1984 የሚሆኑት ትምህርት ቤቶች አሁን ባለው በክልሉ ባለው ጦርነት ጉዳት የደረሰባቸው እነደሆኑም ተነግሯል።


እስከ አሁን 2445 ትምህርት ቤቶች ዝግ ናቸው፣ 9 የአማራ ክልል ወረዳዎች ተማሪ እስካሁን አልመዘገቡም ተብሏል።


የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታዋ ህብረተሰቡ ልጆቹን ቅድሚያ ወደ ትምህርት ቤት ሊልክ ይገባል ይህ መታሰብ አለበት ሲሉ ተናግረዋል።


ተማሪዎችን ከትምህርት ገበታ ማስቀረት ሃገርንም ትውልድንም የሚገድል ነው ብለዋል።


በረከት አካሉ


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…


Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page