ሐምሌ 26 2017 - ኒዩሮ ሳይንስ ለሥራ ፈጠራ(ቅጽ ፩) እና የኒዩሮ አመራር ሳይንስ (ቅጽ ፪) የተሰኙ መፃህፍት ለገበያ ቀርበዋል
- sheger1021fm
- Aug 2
- 1 min read
ስራ ለመጀመር፣ ቢዝነስን ለማቀላጠፍና ለመምራት እንዲሁም ከስኬት ለማድረስ ጥልፍልፍ አሰራሮች፣ የእውቀትና የልምድ ማጣት የብዙዎች ችግር ሆኖ ይታያል።
ለዚህ ደግሞ መላ የሚያቃብሉ በሁለት ቅፅ የተፃፉ መፃህፍት ለገበያ ቀርበዋል።
መፃፎቹ ኒዩሮ ሳይንስ ለሥራ ፈጠራ(ቅጽ ፩) እና የኒዩሮ አመራር ሳይንስ (ቅጽ ፪) ናቸው።
ደራሲው ደግሞ ያሬድ ኢሳያስ(ዶ/ር) ይባላሉ።
የረቀቀውን የሰውን ልጅ አዕምሮ ተጠቅሞ በጎ ፍሬ ለመልቀም፣ የተሻለውን አጥንቶ ለመጓዝ ይጠቅማሉ ተብሏል።

ኩባንያ የሚያስተዳድረው፣ የሀገር ሀላፊነት ያለበት፣ ግለሰቦች፣ ስራ ፈጣሪዎች የአመራር ውጤት እንዲያገኙ ይረዳሉም ተብሏል።
ኒውሮ ሳይንስለስራ ፈጠራ አእምሮአችን እንዴት እንደሚሠራ በማብራራት ለንግድ ሥራ ጥቅም ሊውል የሚችል ወሰን አልባ ዕምቅ የአእምሮአችንን ችሎታ እንዴት አውጥተን መጠቀም እንደምንችል ግንዛቤ ያስጨብጠናል ተብሎለታል።
እንዴት የራስህን የንግድ ሥራ፣ ግንኙነቶችን እና ትርጉም ያለውና ሕይወት መጀመር እና ማሳደግ እንደሚቻል መፃህፉ ያስረዳል ሲባል ሰምተናል።
አዕምሮ ራሱ ግን ምንድን ነው? እንዴትስ ለንግድ ስኬት ጥቅም ላይ መዋል ይቻላል? ውጫዊ ችግሮችንስ እንዴት መቆጣጠር ይቻላል? ከመፃህፎቹ የሚገኙ ሌሎች ጉዳዮች ናቸው።
በሁለት ቅፅ የቀረቡትን መፃህፍት የፃፉት ዶ/ር ያሬድ ኢሳያስ የበርካታ ስኬታማ ኩባንያዎች መሥራች፣ ባለቤትና በኪይ ዌስት ዩኒቨርሲቲ መምህር መሆናቸው ተነግሯል።

ደራሲው ለመፃፍ የተነሱትም እስካሁን ባደረጓቸው ሰፊ ሳይንሳዊ ጥናቶች እና የራሳቸውን ንግድ ሥራ በመምራት ካካበቱት ተሞክሮዎች ያረጋገጡትን መሆኑ ተጠቅሷል።
መፃፎቹ በትናንትናው ዕለት በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ዋናው ጊቢ ራስ መኮንን አዳራሽ ሲመረቅ ንግግር ያደረጉ የቢዝነስ ሰዎች፣የዩኒቨርስቲ መምህራን ፣ደራሲያን እና ሌሎች መፃህፍቱ ስራ ለመጀመር ለሚያስቡ፣ለሚሰሩ ሀላፊነት ላለባቸውን መንገዳቸው ወደዚያው የሆኑ ሁሉ እንዲያነቧቸው ጋብዘዋል።
መፃፎቹ በሶስት ቋንቋዎች ማለትም በአማርኛ፣ በኦሮምኛ እና በእንግሊዝኛ መዘጋጀታቸው ተጠቅሷል።
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
📌 Telegram; https://t.me/ShegerFMRadio102_1
📌 YouTube: https://shorturl.at/P4mpX
📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s












Comments