top of page

ሐምሌ 23፣2016 - ሕዝባዊ ወያኔ ሐርነት ትግራይ(ህወሐት) ህጋዊ ሰውነቴ ይመለስልኝ ሲል ጥያቄ አቀረበ

  • sheger1021fm
  • Jul 30, 2024
  • 1 min read

ሕዝባዊ ወያኔ ሐርነት ትግራይ(ህወሐት) ህጋዊ ሰውነቴ ይመለስልኝ ሲል ጥያቄ አቀረበ፡፡


የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ህጋዊ ሰውነቱን እንዲመልስለት በደብዳቤ ጠይቋል፡፡


የሰሜኑን ጦርነት ተከትሎ ሽብርተኛ ተብሎ ተፈርጆ የነበረው ሕውሀት በምርጫ ቦርድም ህጋዊ ሰውነቱ ተሰርዞ እንደነበር በደብዳቤው አስታውሷል፡፡


ይሁንና ከፕሪቶሪያው ስምምነት በኋላ ከአሸባሪነት ዝርዝር መፋቁን በማስታወስ ከፌዴራል መንግስትም ጋር በመግባባት እየሰራሁ ነው ያለው ሕወሃት ቦርዱ የድርጀቱን ህጋዊ ሰውነት ወደ ነበረበት እንዲመልስ የሚጠይቅ ደብዳቤ አስገብቷል፡፡

ree

ደብዳቤው ለህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት እና ለጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤትም በግልባጭ እንዳስገባ ከሰሞኑ ለብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የፃፈው ደብዳቤ ያመለክታል፡፡


ሕወሃት ህጋዊ ሰውነቱን መልሶ ካላገኘ ዋጋ እንደሌለው እና ህጋዊ ሳይሆን የሚያደርጋቸው እንቅስቃሴዎች ወደ ዳግም ጦርነት ሊያስገቡ እንደሚችሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ከተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር በነበራቸው ውይይት መናገራቸው ይታወሳል፡፡


የኢትዮጵያ የምርጫ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባ እና የምርጫ ሥነ - ምግባር አዋጅም ሕወሃት ዳግም ህጋዊ እውቅና እንዲያገኝ የሚያስችለው ሆኖ መሻሻሉ እና በሕዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት መፅደቁም አይዘነጋም፡፡


ትዕግስት ዘሪሁን

Recent Posts

See All
ህዳር 25 2018 የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ የሁለት ሚኒስትሮችን እና የአንድ ዋና ስራ አስፈጻሚ ሹመትን አፀደቀ።

ሹመታቸው በምክር ቤቱ የፀደቀላቸው የሠላም ሚኒስትሩ አቶ መሃመድ እድሪስ፤ የግብርና ሚኒስትሩ አቶ አዲሱ አረጋ እንዲሁም የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ቢንያም ኤሮ ናቸው። አቶ መሃመድ እድሪስ የሰላም ሚኒስትር ሆነው በጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ተሹመው  ስራ የጀመሩት ኀዳር 18 ቀን

 
 
 

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page