ሐምሌ 17 2017 - የጊዜያዊ አስተዳደሩ ከሃይማኖት ተቋማት ጉባዔ ጋር በምን ምን ጉዳዮች ላይ መከረ?
- sheger1021fm
- Jul 24
- 1 min read
ከቀናት በፊት ወደ መቀሌ አቅንቶ ከጊዜያዊ አስተዳደሩ ጋር የመከረው #የሃይማኖት_ተቋማት_ጉባኤ ልዑክ፤ የክልሉ አስተዳደር ሰላምን እንዲፀና መጠየቁ ተነገር፡፡
ጊዜያዊ አስተዳደሩ ለልዑክ ቡድኑ በክልሉ በኩል የሚነሳ ጦርነት እንደሌለ አረጋግጬላቸዋለሁ ብሏል፡፡

ሰኔ 26 ቀን 2017 ዓ.ም በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀርበው ከምክር ቤት አባላት ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽ እና ማብራሪያ የሰጡት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የትግራይ ክልልን ጉዳይ በውይይት መፍታት እንደሚቻል ጠቁመው በክልሉ ባሉ ሀይሎች ዘንድም ጦርነት እንደማያስፈልግ መታወቅ አለበት ማለታቸው ይታወሳል፡፡
በክልሉ ዳግም ጦርነት እንዳይነሳም የሃይማኖት አባቶች፣ ኤምባሲዎች እና ሌሎች ጉዳዩ የሚመለከታቸው አካላት በአስቸኳይ የድርሻቸው እንዲወጡ አሳስበው ነበር፡፡
ይህን ተከትሎም በኢትዮጵያ ሃይማኖት ተቋማት ጉባዔ የሚመራ ልዑክ ባለፈው ሳምንት ወደ #መቀሌ ማቅናቱ እና ወይይት አድርጎ መመለሱ ይታወቃል፡፡
የጊዜያዊ አስተዳደሩ ከሃይማኖት ተቋማት ጉባዔ ጋር በምን ምን ጉዳዮች ላይ እንደመከረ ጠይቀናል፡፡
አቶ ቃላይ አሰፋ የክልሉ ብዝሃነት እና የህዝቦች ግንኙነት ፅህፈት ቤት ሀላፊ ናቸው፡፡
አቶ ቃላይ በጋራ አራት የውይይት መድረኮች ከሃይማኖት ተቋማት ልዑክ ጋር ማካሄዳቸውን ተናግረው ውይይቱም የተስማማንበት ነበር ሲሉ አስረድተዋል፡፡
የሃይኖማት አባቶች ሰላምን አጽኑ፤ ለሰላምም ስሩ ብለውናል እኛም እሺ ብለን ተቀብለናቸዋል ያሉት አቶ ቃላይ ለሰላም እየሰራን እንዳለም ነግረናቸዋል ብለዋል፡፡
ተፈናቃዮች ወደ ቀድሞ ቦታቸው እንዲመለሱ፣ በሀይል የተያዙ መሬቶች እንዲለቀቁ፣ በፌደራል መንግስት እና በሕውሃት መካከል ንግግሮች እንዲቀጥሉ እና ለግጭት ምክንያት የሆኑ ችግሮች በንግግር እንዲፈቱ ጊዜያዊ አስተዳደሩ ለሃይማኖት አባቶች ሀሳብ ማቅረቡን ሰምተናል፡፡
ያሬድ እንዳሻው
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
📌 Telegram; https://t.me/ShegerFMRadio102_1
📌 YouTube: https://shorturl.at/P4mpX
📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s












Comments