top of page

ሐምሌ 17 2017 - በከፍተኛ ማዕረግ የሚመረቁ ተማሪዎች ለመስተማር ከፈቀዱ ስልጠና ወስደው መምህር እንዲሆኑ ለማድረግ የሚያስችል አሰራር

  • sheger1021fm
  • Jul 24
  • 1 min read

ከዩኒቨርሲቲዎች በከፍተኛ ማዕረግ የሚመረቁ ተማሪዎች በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ለመስተማር ከፈቀዱ ስልጠና ወስደው መምህር እንዲሆኑ ለማድረግ የሚያስችል አሰራር ከ2018 ጀምሮ ወደ ስራ ሊያስገባ መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር ተናገረ፡፡


አማራጭ የመምህራን ስልጠና ፕሮግራም በሚል ወደ ስራ ይገባል የተባለው አሰራር የ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ላይ የሚታየውን የመምህራን እጥረት ለመቅረፍ ይረዳል ብሏል ትምህርት ሚኒስቴር፡፡


ይህ የተባለው የክረምት ልዩ የመምህራንና የትምህርት ቤት አመራሮች የአቅም ማሻሻያ ስልጠና ለማስጀመር በማሰብ ከ30 ዩኒቨርሲቲዎች ለተውጣጡ አሰልጣኝ መምህራን እየተሰጠ ያለው ስልጠና በተጀመረበት ወቅት ነው፡፡

ree

የትምህርት ሚኒስትር ድኤታ አየለች እሸቴ ለመጀመሪያ ጊዜ በተካሄደው የ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የተፈጥሮ ሳይንስ መምህራን ስልጠና ያልተካፈሉ መምህራን፣ የማህበራዊ ሳይንስ መምህራን፣ የስራና ተግባር ትምህርት መምህራን በስልጠናው ላይ ተሳታፊ ይሆናሉ ብለዋል፡፡


ባለፈው ዓመት ለመጀመሪያ ጊዜ በተሰጠው ስልጠና ልምድ አግኝተናል ያሉት ወ/ሮ አየለች እሸቴ ለ2ኛ ጊዜ የሚሰጠው የአቅም ማሻሻያ ስልጠና መምህራኑ በሚያስተምሩት የትምህርት ዘርፍ ላይ ጥሩ ግንዛቤ እንዲኖራቸው ለማድረግ ተዘጋጅተናል ሲሉም ጠቅሰዋል፡፡


ትምህርት ሚኒስቴር ከ2018 ጀምሮ በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የሚታየው የመምህራን እጥረት ለመቅረፍና ዘርፉን ይበልጥ ለማሳደግ በማሰብ አማራጭ የመምህራን ስልጠና ፕሮግራም አዘጋጅቷል ያሉት ደግሞ በትምህርት ሚኒስቴር ‎የመምህራንና የትምህርት አመራሮች ልማት መሪ ስራ አስፈፃሚ ሙሉቀን ንጋቱ(ዶ/ር) ናቸው፡፡


በከፍተኛ ነጥብ ተመርቀው የሚወጡ ተማሪዎች መምህር የመሆን ፍላጎች ካላቸው ትምህርት ሚኒስቴር የሚያዘጋጀውን ፈተና ካለፉ የሚፈለገው ስልጠና ተሰጥቷቸው በመምህርነት እንዲሰማሩ ይደረጋል ብለዋል፡፡


ለዚህ ፕሮግራም ጅማሮ አሁን ላይ 6 ዩኒቨርሲቲዎች ዝግጅት እያደረጉ መሆኑን ሰምተናል፡፡


በዘንድሮው የመምህራንና የትምህርት ቤት አመራሮች የአቅም ማሻሻያ ስልጠና 84,000 ሰልጣኞች ይካፈላሉ፡፡


ከ30 ዩኒቨርሲቲዎች 630 የሚሆኑ መምህራን ስልጠናውን ይሰጣሉ ተብሏል፡፡


ስልጠናው ሀምሌ 28 ይጀመራል፡፡


በረከት አካሉ


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…




Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page