top of page

ሐምሌ 11 2017 የውጪ ሀገራት ወሬዎች

  • sheger1021fm
  • Jul 18
  • 2 min read

በብሪታንያ የመራጭ ድምፅ ሰጭዎች እድሜ ዝቅ ሊደረግ ነው፡፡


እስካሁን በአገሪቱ የሚሰራበት የመራጮች ዝቅተኛ እድሜ 18 እንደሆነ አልጀዚራ አስታውሷል፡፡


አሁን ግን የድምፅ ሰጭዎቹን እድሜ ወደ 16 አመት ዝቅ ለማድረግ መታሰቡ ታውቋል፡፡

ree

በስልጣን ላይ የሚገኘው የሌበር መንግስት የመራጮችን ድምፅ መስጫ እድሜ ዝቅ ለማድረግ የታለመ ሀሳብ ማቅረቡ ተሰምቷል፡፡


የፖለቲካ ማህበሩ ይሄን ሀሳብ በቀዳሚው ምርጫ ወቅት ቃል በመግባት ሲቀሰቅስበት እንደነበር ለትውስታ ተጠቅሷል፡፡


የመራጭ ድምፅ ሰጭዎችን እድሜ ወደ 16 አመት ዝቅ ማድረጊያው ሀሳብ የአገሪቱን ፓርላማ ይሁንታ የሚሻ ነው ተብሏል፡፡



የሮማ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ እስራኤል በጋዛ በሚገኝ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ላይ ድብደባ መፈፀሟ በእጅጉ አሳዝኖኛል አሉ፡፡


በእስራኤል የአየር ጥቃት በጥቂቱ ሶስት ሰዎች እንደተገደሉ አናዶሉ ፅፏል፡፡


በርካቶች ደግሞ አካላዊ ጉዳት ደርሶባቸዋል ተብሏል፡፡


በጥቃቱ የአካል ጉዳት ከደረሰባቸው መካከል የቤተ ክርስቲያኒቱ አገልጋዮችም ይገኙበታል ተብሏል፡፡


ሊዮ 14ኛ በተደጋጋሚ በጋዛ ሰርጥ የተኩስ አቁም እንዲደረግ ሲማፀኑ መቆየታቸውን መረጃው አስታውሷል፡፡


እስራኤል የጋዛ የጦር ዘመቻዋን ከጀመረች ከ21 ወራት በላይ ሆኗታል፡፡


የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ኔታንያሁ በጋዛው የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ላይ በተፈፀመው ድብደባ አዝኛለሁ ማለታቸው ተሰምቷል፡፡



ትናንት በቶጎ በተካሄደው ማዘጋጃ ቤታዊ እና የአካባቢ ምክር ቤቶች አባላት ምርጫ ህዝባዊ ተሳትፎው በእጅጉ የሳሳ ነበር ተባለ፡፡


ምርጫው የተካሄደው ባለፈው ወር የተደረገውን ከፍተኛ ፀረ መንግስት ተቃውሞ ተከትሎ እንደሆነ አልጀዚራ አስታውሷል፡፡


ሰልፉ ከባድ ግጭት የደረሰበት ሲሆን ሰባት ሰልፈኞችም የተገደሉበት ነበር፡፡


የተቃውሞ ሰልፉ የተደረገው የአገሪቱን መሪ ፋውሬ ንያሲምቤን እድሜ ልካቸውን ስልጣን እንደያዙ እንዲዘልቁ የሚያስችላቸው ህገ መንግስታዊ ማሻሻያ መደረጉን በመቃወም ነው ተብሏል፡፡


ሕጉን ያፀደቀው ፓርላማ ፋውሬ ንያሲምቤ የሚመሩት ገዢ የፖለቲካ ማህበር አባላት የሚበዙበት እንደሆነ በመረጃው ለትውስታ ተጠቅሷል፡፡


የትናንቱም አካባቢያዊ ምርጫ ከወር በፊት የተካሄደው ከባድ የተቃውሞ ስሜት የዞረ ድምር ያልለቀቀው ነበር ተብሏል፡፡



የቡርካናፋሶ ወታደራዊ መንግስት ከእንግዲህ የምርጫ ኮሚሽን አያሻንም አለ፡፡


የወታደራዊ መንግስቱ የበላይ ሻምበል ኢብራሂም ትራኦሬ የምርጫ ኮሚሽኑ ሀላፊነት ላይ መቆየቱ ትርፉ የአገሪቱን ገንዘብ ማባከን ብቻ ነው ማለታቸውን ቢቢሲ ፅፏል፡፡


ከእንግዲህም ምርጫን በበላይነት የመምራቱ ተግባር በአገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ እንደሚመራ ትራኦሬ ተናግረዋል፡፡

በአገሪቱ ባለፈው አመት መከናወን የነበረበት ምርጫ በደፈናው ከተራዘመ ቆይቷል ተብሏል፡፡


የአገሪቱ የሽግግር ጊዜም ለተጨማሪ 4 አመታት እንዲራዘም ተደርጓል፡፡


ሻምበል ኢብራሂም ትራኦሬ የሽግግሩ ጊዜ እስኪያበቃ በአገር መሪነታቸው እንደሚቀጥሉ መረጃው አስታውሷል፡፡



ፈረንሳይ በሴኔጋል የነበሯትን ሁለት የመጨረሻ የጦር ሰፈሮች ለአገሪቱ ጦር አስረከበች፡፡


ፈረንሳይ የጦር ሰፈሮቹን ለሴኔጋል ያስረከበችው የሁለቱ አገሮች ከፍተኛ የጦር ሹሞች በተገኙበት በተከናወነ ስነ ስርዓት እንደሆነ ፍራንስ 24 ፅፏል፡፡


የአሁኑ የሴኔጋል ፕሬዘዳንት ባሲሩ ፌይ ባለፈው አመት በምርጫ እንዳሸነፉ በአገሪቱ የፈረንሳይ የጦር ቆይታ እንዲያበቃ ጠይቀው እንደነበር ለትውስታ ተጠቅሷል፡፡


ሴኔጋል ነፃነቷን ካገኘች አንስቶ ፈረንሳይ በምዕራብ አፍሪካዊቱ አገር የጦር ሰፈሮቿን ተክላ ቆይታለች፡፡


አውሮፓዊቱ አገር ቀደም ሲልም በሌላኛዋ ምእራብ አፍሪካዊት አገር ኮትዲቭዋር የነበሯትን የጦር ሰፈሮች ለአገሪቱ መንግስት አስረክባለች፡፡


ማሊ ፣ ቡርኪናፋሶ እና ኒጀርም የፈረንሳይ ጦር ሰፈሮች እና ወታደሮች አያሹንም ያሉ አገሮች ናቸው፡፡


የኔነህ ከበደ


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…




Recent Posts

See All
ጥቅምት 20 2018 - የፍትህ ስርዓት ችግር ምክንያት ስራው ላይ እክል እየገጠመው መሆኑን የኢትዮጵያ ህዝብ እምባ ጠባቂ ተቋም ተናገረ

የሚሰጣቸውን ምክረ ሃሳቦች ያለ በቂ ምክንያት የማይፈፅሙ ተቋማት በህግ እንዲጠየቁ ለማድረግ ቢሞክርም ባለው የፍትህ ስርዓት ችግር ምክንያት ስራው ላይ እክል እየገጠመው መሆኑን የኢትዮጵያ ህዝብ እምባ ጠባቂ ተቋም ተናገረ፡፡ ተቋሙ የአስተዳደር በደል ደረሰብን እምባችን ይታበስልን የሚሉ አቤት ባዮችን ቅሬታ በመቀበል

 
 
 

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page