top of page

ህንድ ኢትዮጵያን ጨምሮ በመላው አፍሪካ የሚገኙ ዜጎቿን አቅም ተጠቅማ የህንድና አፍሪካ ግኑኝነትን ለማጠናከር በብርቱ ለመመስራት ማሰቧ ተሰማ።

  • 5 hours ago
  • 2 min read

መጋቢት 15/2018


ህንድ ኢትዮጵያን ጨምሮ በመላው አፍሪካ የሚገኙ ዜጎቿን አቅም ተጠቅማ የህንድና አፍሪካ ግኑኝነትን ለማጠናከር በብርቱ ለመመስራት ማሰቧ ተሰማ።


ይህንን ለማድግ ያግዛል የተባለ ውይይት አዲስ አበባ በሚገኘው የህንድ ኤምባሲ ትናንት ምሽት ተደርጓል።


ህንድ ኢትዮጵያ ጨምሮ በመላው አፍሪካ 3 ሚሊዮን ዲያስፖራ እንዳላት ተነግሯል።

የሀገሪቱ ዜጎች ኒው ዴሊ ከአፍሪካ ሀገራት ጋር ያላትን ግኑኝነት ለማጠናከር በምን በምን ዘርፎች ቢሰሩ ይሻላል፣ምን ጉድለት አለ? ምንስ ፈተናዎች አሉ በሚለው ላይ በየዘርፉ ገለፃ ተደርጎ ውይይት ተካሂዷል።


በሰው ሰራሽ አስተውህሎት ወይም AI ዘርፍ ህንድ በአለም ዙሪያ ተፅዕኖ እያሳደረች መሆኑ የተነገረ ሲሆን በአፍሪካም በተለይም በAI የታገዘ በግብርና፣ ጤና፣ ቴክኖሎጂ ዘርፎች ዜጎቿ በስፋት መሰማራት የሚችሉባቸው ዘርፎች መሆናቸው ተጠቅሷል።


ሳይበር ደህንነት፣ ስፔስ ቴክኖሎጂ ዘርፎችም በዚህ ረገድ ያሉ ሌሎች ጉዳዮች መሆናቸው ተነስቷል።


የመብራት፣ የኢንተርኔት ተደራሽነት ውስን መሆን እንዲሁም የሰው ሰራሽ አስተውህሎት የሚመራበት ህግ አብዛኛው የአፍሪካ ሀገር አለመኖር እንደ ችግር ተነስቷል።

ሌላው በአፍሪካ የሚገኙ የህንድ ዲያስፖራዎች የህንድና የአፍሪካን ግኑኝነት ለማጠናከር በብርቱ ለመስራት የለዩት ዘርፍ ማዕድን ነው።


30 በመቶው የአለም የማዕድን ክምችት በአፍሪካ ቢገኝም አህጉሪቱ ለገበያ የምታቀርበው ግን እሴት ሳይጨመርበት ጥሬውን እንደሆነ ተነግሯል።


ይህም የስራ እድል እንዳይፈጠር፣ ኢንዱስትሪ እንዳይስፋፋ፣ አህጉሪቱም ከማዕድን ሀብቷ እንዳትጠቀም ማድረጉ ተጠቅሷል።


በአፍሪካ የሚገኙ ህንዳውያን በማዕድን ዘርፍ የአፍሪካ ሀገራትን ተቋማት አቅም ማሳደግ ላይ ሊበረቱ እንደሚገባ ተነስቷል።


ፕላስቲክ እና ጨርቅ ጨርቅ፣ግብርና ፣መድሀኒት ፣ፊልም ሌሎች በአፍሪካ የሚገኙ ህንዳውያን በስፋት ሊሰማሩባቸውና ሀሪቱም ከአፍሪካ ሀገራት ጋር ያላትን ግኑኝነት ለማጠናከር የሚያግዟት ዘርፎች መሆናቸውን ውይይቱ ሲደረግ ሰምተናል።

በውይይቱ ላይ በአትዮጵያ የህንድ አምባሳደር አኒታ ኩማር ፣የኢንዱስትሪ ሃለፊዎች አን ሌሎች ተገኝተዋል፡፡


ህንድና ኢትዮጵያ የረጅም አመታት ግኙኝነት ያላቸው ሲሆን ግኑኝነታቸው ዘመናዊ ቅርጽ የያዘው ህንድ ከቅኝ ግዛት ነጻ ከወጣች ጀምሮ ነው፡፡ ይህም ከ75 አመታት በላይ ሆኖታል፡፡


ሁለቱ አገራት በተለያዩ መስኮች በትብብር እየሰሩ ነው፡፡


በንግድ፣በሳይንስና ቴክኖሎጂ፤ አነስተኛ ግድብ እና መስኖ፣ህክምና ዘርፎች በትብብር የሚሰሩባቸው ዘርፎች መካከል ይጠቀሳሉ፡፡


ባለፈው አንድ ዓመት ውስጥ ኢትዮጵያ አና ህንድ 550 ሚሊዮን ዶላር የንግድ ልውውጥ ማድረጋቸውን መረጃዎች ያሳያሉ፡፡


በአሁኑ ሰዓትም ከ675 ባለይ የህንድ ኩባንያዎች 6.5 ቢሊዮን ዶላር ኢንቨስት አድርገው በኢትዮጵያ እየሰሩ ነው፡፡


በቅርቡ የህንዱ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ ኢትዮጵያን መጎብኘታቸውነ ተከትሎ የሁለት ሀገራት ግኑኝነት ወደ ስትራቴጂካዊ አጋርነት እንዲያድግ አስችሏል መባሉ ይታወሳል።


ንጋቱ ሙሉ


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…


YouTube : https://shorturl.at/18TS1

WhatsApp : https://shorturl.at/8vwRx

X :- https://x.com/shegerfm?s=2

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page