top of page

ህግ አውጪ ተቋማት በጥናትና ምርምር ለመደገፍ ይሰራል የተባለለት ተቋም ስራ መጀመሩን ተነግሯል

  • sheger1021fm
  • 17 minutes ago
  • 1 min read

ህዳር 4 2018 

 

እንደ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ያሉ ህግ አውጪ ተቋማት በጥናትና ምርምር ለመደገፍ ይሰራል፣ ለሰላምና ዲሞክራሲ ግንባታ እገዛ ያደርጋል የተባለለት ተቋም ስራ መጀመሩን ተነግሯል፡፡

 

እንደራሴዎች በተገኙበት ስራ መጀመሩን የተናገረው ብሪጅ ሪሰርችና ኢኖቬሽን የተባለ ድርጅት በኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙ 18 የህግ አውጪ ምክር ቤቶችን በገለልተኝነት ሙያዊ የሆነ የአቅም ግንባታ ስራዎችን እሰራለሁ ብሏል፡፡፡

 

ህግ አውጪዎች ያሉባቸው ክፍተቶች ምንድናቸው? የሚለውን በመለየት በጥናትና ምርምር ለማገዝ መቋቋሙን የነገሩን የድርጅቱ ዋና ስራ አስፈፃሚ ቃለ አብ ታደሰ(ዶ/ር) ናቸው፡፡

 

ree

ተቋሙ ወደ ስራ ከገባ የመጀመሪያ የሆነውን ጥናት ቢያደርግም ወደፊት ሌሎች ምርምርና ጥናት የሚደረግባቸው ስራዎችን ከምክር ቤቱ ጋር እንደሚያደርግም አስረድተዋል፡፡

 

ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ የሲቪክ ማህበራትና ምሁራን በዚህ በምክር ቤት ዙሪያ የሚደረግ ጥናትና ምርምርን ገሸሽ ያደረጉት ጉዳይ ነው የሚሉት ዋና ስራ አስፈፃሚው የመመረቂያ ጥናታዊ ጽሁፎችን ከማድረግ በዘለለ ክፍተቶችን ሲሞሉ አይታዩም ብለዋል፡፡

 

ree

የምክር ቤት አባሉ አቶ ፍሬው ተስፋዬ በበኩላቸው የምርምር እና የጥናት ተቋማት ገለልተኛ ሆነው የሀገርን ብሔራዊ ጥቅም እና የህዝብንም ተጠቃሚነት በመጠበቅ ሃሳባቸውን ነጻ ሆነው ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል ያሉ ሲሆን  ምክር ቤቱም ይህንን ውጤት እንደ ግብዓት እየተጠቀመ አሰራሩን ለማሻሻል ሊጠቀምበት ይገባል ብለዋል፡፡

 

ብሪጅ ሪሰርች ኢኖቬሽን ከምርምርና ጥናት ስራው በተጨማሪ በምስራቅ አፍሪካ የሰላምና የልማት ስራዎች ላይ እንደሚሳተፍም ሰምተናል፡፡

 

የምርምርና የጥናት ተቋሙን ያቋቋሙት የረዥም ዓመት ልምድ ያላቸው በህግ፣ በፖለቲካል ሳይንስ፣ በታሪክ ላይ ጥናትና ምርምር በሚያደርጉ ምሁራን እንደሆነ ተነግሯል፡፡

 

ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ…

 

ማርታ በቀለ

 

የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

👇👇👇

 

Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page